عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
بَيْنَمَا نَحْنُ فِي الْمَسْجِدِ مَعَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِذْ جَاءَ أَعْرَابِيٌّ، فَقَامَ يَبُولُ فِي الْمَسْجِدِ، فَقَالَ أَصْحَابُ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: مَهْ مَهْ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَا تُزْرِمُوهُ، دَعُوهُ» فَتَرَكُوهُ حَتَّى بَالَ، ثُمَّ إِنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ دَعَاهُ فَقَالَ لَهُ: «إِنَّ هَذِهِ الْمَسَاجِدَ لَا تَصْلُحُ لِشَيْءٍ مِنْ هَذَا الْبَوْلِ، وَلَا الْقَذَرِ إِنَّمَا هِيَ لِذِكْرِ اللهِ عَزَّ وَجَلَّ، وَالصَّلَاةِ وَقِرَاءَةِ الْقُرْآنِ» أَوْ كَمَا قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: فَأَمَرَ رَجُلًا مِنَ الْقَوْمِ فَجَاءَ بِدَلْوٍ مِنْ مَاءٍ فَشَنَّهُ عَلَيْهِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 285]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
«እኛ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ተቀምጠን ሳለ ድንገት አንድ የገጠር ሰው መጣና መስጂድ ውስጥ መሽናት ጀመረ። የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ባልደረቦችም "አተ! አተ!" አሉት። የአላህ መልክተኛም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "አታቋርጡት ተዉት!" አሉ። ሸንቶ እስኪያጠናቅቅም ተዉት። ቀጥሎ የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠሩትና እንዲህ አሉት: "እነዚህ መስጂዶች ለዚህ ሽንትና ቆሻሻ አይበጁም። እነዚህ የሚበጁት አላህን ለማውሳት፣ ለሶላትና ቁርአንን ለመቅራት ነው።" አሉት። ወይም የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ይህን የመሰለ ንግግር ተናገሩት። አንድን ሰው ውሃ የሞላ ባልዲ ይዞ እንዲመጣ አዘዙና እላዩ ላይ ደፉበት።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 285]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - መስጂዳቸው ውስጥ ከባልደረቦቻቸው ጋር ነበሩ። አንድ ባላገር ከገጠር መጣና የመስጂዱ ጎን ዘንድ ተቀምጦ መሽናት ጀመረ። ሶሓቦችም "አተ አቁም! ተው!" በማለት አስጠነቀቁት። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ተዉት! ሽንቱን አታቋርጡት።" አሉ። እስኪያጠናቅቅም ድረስ ተዉት።
ከዚያም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠርተው እንዲህ አሉት: መስጂዶች ለሽንትና ለቆሻሻ አይነቶች አይበጁም። መስጂድ የሚበጀው አላህን ለማውሳት፣ ለሶላት፣ ቁርአንን ለመቅራትና ለመሳሰሉት ነው። ቀጥለው ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - አንድን ሶሓባ በውሃ የተሞላ ባልዲ ይዞ እንዲመጣ አዘዙና በቀላሉ ሽንቱ ላይ ደፉበት።