1. ዋና ገጽ
  2. ምድቦች
  3. ዐቂዳ (እምነት)

ሐዲሥ መላዕክቶች ውሻና ስዕል ወዳለበት ቤት አይገቡም።

عَنْ أَبِي طَلْحَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لاَ تَدْخُلُ المَلاَئِكَةُ بَيْتًا فِيهِ كَلْبٌ وَلاَ صُورَةٌ».

ከአቡ ጦልሓ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"መላዕክቶች ውሻና ስዕል ወዳለበት ቤት አይገቡም።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3322

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የእዝነት መላዕክቶች ውሻና ነፍስ ያላቸው የፍጡራን ስዕል ወዳለበት ቤት እንደማይገቡ ተናገሩ። ይህም ነፍስ ያለበት ምሥል አስከፊ ወንጀል ስለሆነ፤ ከአላህ አፈጣጠር ጋር መፎካከር ስለሆነ፤ የሽርክ መዳረሻም ስለሆነ፤ አንዳንዶቹ ምሥሎችም ከአላህ ውጪ የሚመለኩ ምሥሎች ስለሆኑ ነው። ውሻ ያለበት ቤት ከመግባት የመቆጠባቸው ምክንያት ደግሞ: በብዛት ነጃሳ ስለሚመገብ፤ አንዳንዶቹም ሸይጧን ተብለው ስለተጠሩ ነው። መላዕክት ደግሞ የሸይጧን ተቃራኒ ናቸው። በተጨማሪ የውሻ ሽታ አፀያፊ ስለሆነ ነው። መላዕክት ደሞ መጥፎ ሽታን ይጠላሉ። ስለዚህ ውሻን ማሳደግ ተከለከለ። የሚያሳድግ ሰውም የእዝነት መላዕክት ቤቱ ባለመግባታቸው፤ ለቤቱ ዱዓእ ባለማድረጋቸው፤ ለርሱ ምህረት ባለመጠየቃቸው፤ ለርሱና ለቤቱ በረከት ባለመጠየቃቸው፤ የሸይጧንን ጉዳት ከርሱ ላይ ባለመከላከላቸው ተቀጣ።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. የአደን ውሻ ወይም የከብት ጠባቂ የሆነ ውሻ ወይም የአዝርዕት ጠባቂ የሆነ ውሻ ካልሆነ በቀር ውሻን ማሳደግ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
  2. ስዕል ማስቀመጥ መላዕክት የሚሸሹት ከሆኑ ቆሻሻ ጉዳዮች አንዱ ነው። በአንድ ስፍራ ስዕል መኖሩ እዝነትን እንድንነፈግ ምክንያት ይሆነናል። ውሻም ልክ እንደዚሁ ነው።
  3. ውሻ ወይም ስዕል ያለበት ቤት ውስጥ የማይገቡት መላዕክቶች የእዝነት መላዕክቶች ናቸው እንጂ ስራን የሚመዘግቡና ሌሎች እንደ መልዐከ ሞት የመሰሉ የስራ ድርሻ ያላቸው መላዕክቶች ግን ሁሉም ቤት ይገባሉ።
  4. ግድግዳና ሌሎች ነገሮች ላይ ነፍስ ያላቸውን ፍጡራን ስዕላቸውን ማንጠልጠል ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
  5. ኸጧቢ እንዲህ ብለዋል: «መላዕክት ውሻ ወይም ስዕል ያለበት ቤት የማይገቡት ማስቀመጡ ክልክል የሆኑ ውሻዎችንና ስዕሎችን ነው። ክልክል ያልሆኑ የአደን ውሻ፣ የአዝርዕትና የከብቶች ጠባቂ የሆኑ ውሻዎችን እንዲሁም ምንጣፍ ላይ፣ ትራስ ላይና የመሳሰሉት ላይ የሚኖሩ ስዕሎች ግን በነርሱ ምክንያት መላዕክት ከመግባት አይቆጠቡም።

ትርጉሞችን አሳይ

53 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية