عن أبي الهيَّاج الأسدي قال:
قَالَ لِي ‌عَلِيُّ بْنُ أَبِي طَالِبٍ: أَلَا أَبْعَثُكَ عَلَى مَا بَعَثَنِي عَلَيْهِ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ؟ أَنْ لَا تَدَعَ تِمْثَالًا إِلَّا طَمَسْتَهُ، وَلَا قَبْرًا مُشْرِفًا إِلَّا سَوَّيْتَهُ.

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 969]
المزيــد ...

ከአቢል ሀያጅ አልአሰዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
"ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ለኔ እንዲህ አለኝ: 'የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በላኩኝ ነገር ላይ ልላክህን? ማንኛውም ምስልን (ስታገኝ) ያስወገድከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው፤ ማንኛውም ከፍ ያለ ቀብርንም ያስተካከልከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 969]

ማብራሪያ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሓቦቻቸውን "ምስልን" (እሱም አካል ይኑረውም አይኑረው ነፍስ ያለው ነገር ምስል ነው።) ያስወገዱት ወይም ያወደሙት ቢሆን እንጂ እንዳይተዉት ይልኩ ነበር።
ከፍ ያለ ቀብርንም ከምድር ጋር እኩል ያደረጉትና በላዩ ላይ የተገነባውንም ያወደሙ ወይም ከመሬት ብዙም ከፍ ሳይል አንድ ስንዝር ብቻ ከፍ በማድረግ ያስተካከሉት ቢሆን እንጂ እንዳይተዉት ይልኩ ነበር።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ነፍስ ያላቸው ነገራቶችን ምስል ማድረግ ወደ ሺርክ ስለሚያዳርስ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
  2. ስልጣን ወይም አቅም ላለው ሰው መጥፎን ነገር በእጅ ማስወገዱ መደንገጉን እንረዳለን።
  3. ስዕላ ስእሎች፣ ቅርፃ ቅርፆችና ቀብር ላይ መገንባትን የመሳሰሉ ወደ ጃሂሊያ ዘመን ፈለጎች የሚጠቁሙ ነገሮችን ሁሉ በማስወገድ ላይ የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ጉጉት እንረዳለን።
ትርጉሞችን አሳይ
ቋንቋ: الإنجليزية الأوردية الإسبانية ተጨማሪ (64)