+ -

عَن أَبي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«الْحَلِفُ مَنْفَقَةٌ لِلسِّلْعَةِ، مَمْحَقَةٌ لِلرِّبْحِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1606]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
"መሃላ ሸቀጥን ተፈላጊ የሚያደርግ (የሚያዋድድ)፤ ትርፍን (በረከት) ደግሞ የሚያጠፋ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1606]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እውነተኛ ሆኖም ቢሆን በመሸጥና በመግዛት ወቅት ከመማልና መሃላን ከማብዛት አስጠነቀቁ። መሀላ ሸቀጡና እቃው እንዲፈለግ ምክንያት እንደሆነ ነገር ግን የትርፉና የስራውን በረከት የሚያጎልና የሚያጠፋ መሆኑንም ተናገሩ። አላህ በርሱ ላይ የመሰረቅ ወይም የመቃጠል ወይም የመስመጥ ወይም የመዘረፍ ወይም የመነጠቅ ወይም ከዚህ ውጪ ያሉ ገንዘቡ እንዲጠፋ የሚያደርጉ ምክንያቶችን ሊጋርጥበት ይችላል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ፈረንሳይኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በአላህ የመማል ጉዳይ ትልቅ እንደሆነና አስፈላጊ ካልሆነ በቀር እንደማይማል እንረዳለን።
  2. ሐራም ስራ መጠኑ ቢበዛ ራሱ በረከቱ በመነሳቱ መልካም ነገር የለውም።
  3. አልቃሪይ እንዲህ ብለዋል: "የተሰራው በረከት የሚወገደው ወይ ገንዘቡ በሚያጋጥመው ጥፋት ነው፤ ወይም በቅርብ ህይወቱ ለሚጠቅመው ወይም ለመጪው አለም ምንዳ በማያስገኝለት ጉዳይ ወጪ በማድረግ ነው፤ ወይም እርሱ ዘንድ ቢሆንም መጠቀሙን በመነፈግ ነው፤ ወይም የማያመሰግነው ሰው እንዲወርሰው በማድረግ ነው።"
  4. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በንግድ ወቅት መሀላ ማብዛት ክልክል መሆኑን ያስረዳል። መማል ሳያስፈልግ መማል ይጠላልና። በመሃላ ሸቀጥን ማዋደድ ደሞ ጉዳዩን ያብሰዋል። ምንአልባት ገዢ በመሃላው ታግዞ ገዝቶ ሊሆን ይችላልና።"
  5. መሀላ ማብዛት የኢማንና የተውሒድ ጉድለት ነው። ምክንያቱም መሀላ ማብዛት ወደ ሁለት ነገር ያደርሳል: አንደኛው: መሀላውን ወደ መዘናጋትና ቦታ ወዳለመስጠት ሲሆን፤ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ: ወደ ውሸት ነው። መሀላው የበዛ ሰው በውሸት የመማል እድሉ ሰፊ ነው። ስለዚህም መሀላን መቀነስና አለማብዛት ይገባል። ይህንን በማስመልከትም አላህ እንዲህ ብሏል: {መሀላዎቻችሁን ጠብቁ!} [አልማኢዳህ: 89]