عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«أَتَدْرُونَ مَا الْغِيبَةُ؟»، قَالُوا: اللهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ، قَالَ: «ذِكْرُكَ أَخَاكَ بِمَا يَكْرَهُ»، قِيلَ: أَفَرَأَيْتَ إِنْ كَانَ فِي أَخِي مَا أَقُولُ؟ قَالَ: «إِنْ كَانَ فِيهِ مَا تَقُولُ فَقَدِ اغْتَبْتَهُ، وَإِنْ لَمْ يَكُنْ فِيهِ فَقَدْ بَهَتَّهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2589]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፡
"ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።" አሉ። "የምናገረው ነገር ወንድሜ ላይ ካለስ (ሀሜት ይባላልን?)" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም "የምትናገረው ነገር እሱ ላይ ካለ በርግጥ አምተሀዋል። እሱ ላይ ከሌለ ደግሞ በርግጥም ቀጥፈህበታል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2589]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተከለከለውን ሀሜት እውነታ : ሙስሊምን በሌለበት በሚጠላው ነገር ማውሳት መሆኑን አብራሩ። ይህም ተፈጥሯዊውም ሆነ ስነ ምግባሪያዊ ባህሪውን ቢያወሳ ተመሳሳይ ነው። እውሩ ፣ አጭበርባሪ ፣ ውሸታምና የመሳሰሉትን እሱ ላይ የሚገኙ የተወገዙ መገለጫዎችን በማውሳት ማማትን የመሳሰለው ነው።
እሱ ላይ የሌሉ ባህሪያት ከሆኑ ግን የተወሱት ከሀሜትም የባሰ ነው። እሱም መቅጠፍ (ቡህታን) ነው የሚሆነው :- ማለትም በሰው ላይ የሌሉበትን ባህሪያት መቅጠፍ ነው።