+ -

عَن قُطْبَةَ بنِ مَالِكٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ مُنْكَرَاتِ الأَخْلاَقِ وَالأَعْمَالِ وَالأَهْوَاءِ».

[صحيح] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 3591]
المزيــد ...

ከቁጥባህ ቢን ማሊክ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ይሉ ነበር:
"አላህ ሆይ! እኔ ከመጥፎ ስነ ምግባራት፣ ከመጥፎ ስራዎችና ከመጥፎ ዝንባሌዎች በአንተ እጠበቃላሁ።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3591]

ትንታኔ

ከነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና -ዱዓዎች መካከል: (አልላሁመ ኢኒ አዑዙ) አላህ ሆይ! እኔ ወደ አንተ እጠጋለሁ፣ ጥበቃህን እፈልጋለሁ። (ቢከ) ሌላውን ትቼ በአንተ ብቻ (ሚን ሙንከራቲ) አላህና መልክተኛው ከከለከሉት ፀያፍ (አልአኽላቅ) እንደ ምቀኝነት፣ ጥላቻና ኩራት ካሉ ስነ ምግባራት (ወልአዕማል) እንደመሳደብና መዝለፍ ካሉ ፀያፍ ተግባራት (ወልአህዋእ) ሸሪዓን ከሚፃረሩ ነፍስ የሚመኛቸው ከሆኑ ዝንባሌዎች (ባንተ እጠበቃለሁ) ማለት ነው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የዚህን ዱዓ ደረጃና ተወዳጅነት እንረዳለን።
  2. አማኝ የሆነ ሰው ውግዝ ስነምግባራትንና መጥፎ ተግባራትን ለመራቅ ይጥራል። ዝንባሌውን ከመከተልና ስሜት ላይ ከመውደቅም ይጠነቀቃል።
  3. ስነምግባር፣ ስራዎችና ዝንባሌዎች ወደ መጥፎና ጥሩ ለሁለት እንደሚከፈሉ እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ