عَن أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِذَا تَثَاءَبَ أَحَدُكُمْ فَلْيُمْسِكْ بِيَدِهِ عَلَى فِيهِ، فَإِنَّ الشَّيْطَانَ يَدْخُلُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2995]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"አንዳችሁ ያዛጋ ጊዜ ሸይጧን ወደ ውስጡ ስለሚገባ በእጁ አፉን ይያዝ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2995]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በስንፍና ወይም በጥጋብና በመሳሰሉት ምክንያት ሲያዛጋ አፉን የከፈተ ሰው ክፍት እንደሆነ ከተወው ሸይጧን ወደ ውስጡ ይገባልና እጁን አፉ ላይ በማኖር እንዲዘጋው ተናገሩ። እጁን አፉ ላይ ማኖሩ ሲያፋሽግ ሸይጧን እንዳይገባ ይከላከላልና።