+ -

عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«إنَّ الرُّقَى والتَمائِمَ والتِّوَلَةَ شِرْكٌ».

[صحيح] - [رواه أبو داود وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 3883]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
"ማነብነብ (ሩቃ) ፣ ሂርዝ ማንጠልጠልና መስተፋቅር ሽርክ ናቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 3883]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ማድረጉ ሺርክ የሆኑ ሁኔታዎችን ገለፁ። ከነሱም መካከል: -
አንደኛ: ማነብነብ (ሩቃ) :- ይህም የጃሂሊያ ሰዎች ይታከሙበት የነበረውን ሽርክን የሰበሰበ ንግግር ነው።
ሁለተኛ: በጨሌና በመሳሰሉ የተሰሩ ሂርዞችን ማንጠልጠል: ይህም የሰው አይን እንዲከላከል በህፃናት፣ በእንስሶችና በሌሎችም ላይ የሚንጠለጠል ነው።
ሶስተኛ: መስተፋቅር: ይህም ከሁለቱ ጥንዶች መካከል አንዱ ሌላኛውን እንዲያፈቅር ተደርጎ የሚሰራ ነው።
እነዚህ ነገሮች ከሺርክ የሚመደቡ ናቸው። ምክንያቱም ይህ በማስረጃ የፀና ሸሪዓዊ ሰበብም ያልሆነን በተለምዶ የተረጋገጠ ህዋሳዊ ሰበብም ያልሆነን ሰበብ አድርጎ መያዝ ነውና። እንደ ቁርአን መቅራት የመሰለ ሸሪዐዊ ሰበቦችን መጠቀም ወይም በተለምዶ የተረጋገጡ መድሃኒቶችን የመሰለ ህዋሳዊ ሰበቦችን መጠቀም ግን መጥቀምና መጉዳት በአላህ እጅ መሆኑንና እነሱ ሰበብ ብቻ መሆናቸውን ከማመን ጋር እስከሆነ ድረስ መጠቀም ይፈቀዳል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht Azerisht الأوزبكية الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ተውሒድና ዐቂዳችንን ከሚያጎድላቸው ነገር መጠበቅ እንደሚገባ ፤
  2. ሽርካዊ ማነብነቦችን፣ ሂርዝና መስተፋቅርን መጠቀም ክልክል መሆኑን ፤
  3. እነዚህን ሶስት ነገሮች እንደ ሰበብ አድርጎ ማመን ትንሹ ሺርክ ነው። ምክንያቱም ሰበብ ያልሆነን ነገር ሰበብ ማድረግ ነውና። ነገር ግን (ከሰበብም በላይ) በራሷ ትጠቅማለችም ትጎዳለችም ብሎ ካመነ ትልቁ ሺርክ ነው።
  4. ክልክል የሆኑ ሺርካዊ ሰበቦችን መፈፀም መከልከሉን ፤
  5. ሸሪዐዊ ከሆነው ሩቃ በስተቀር ማነብነብ ሺርክ ስለሆነ መከልከሉን ፤
  6. ቀልብ በአላህ ላይ ብቻ ነው ሊንጠለጠል የሚገባው ፤ ጉዳትም ይሁን ጥቅም የሚገኘው አጋር ከሌለው ከሱ ብቻ ነውና። ከአላህ ውጪ መልካምን የሚያመጣ የለም ፤ ከአላህ ውጪ መጥፎን የሚከላከልም የለም።
  7. የሚፈቀደው ሩቃ ሶስት መስፈርቶችን ያካተተ መሆን ይገባዋል: 1- ሩቃው ሰበብ ብቻ እንደሆነና ከአላህ ፍቃድ ውጪ እንደማይጠቅም ማመን፤ 2 - ሩቃው በቁርአን፣ በአላህ ስሞችና ባህሪያት ፣ በነቢያዊ ዱዓዎች፣ ሸሪዐውን በጠበቁ ዱዓዎች ሊሆን ይገባዋል፤ 3 - ሩቃው በግልፅ ቋንቋ ሊሆን ይገባል። የማይገቡ በሆኑ ቋንቋ የሚሰመሩ መስመሮችና ማታለያዎችን የራቀ ሊሆን ይገባል።