عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المؤْمنينَ رَضيَ اللهُ عنها قَالَت:
كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِذَا أَتَى الْمَرِيضَ يَدْعُو لَهُ قَالَ: «أَذْهِبِ الْبَاسَ، رَبَّ النَّاسِ، وَاشْفِ أَنْتَ الشَّافِي، لَا شِفَاءَ إِلَّا شِفَاؤُكَ، شِفَاءً لَا يُغَادِرُ سَقَمًا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2191]
المزيــد ...
ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ወደ ህመምተኛ የሄዱ ጊዜ እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጉለት ነበር: "አዝሂቢልባስ ረበንናስ ወሽፊ አንተ ሻፊ፤ ላ ሺፋአ ኢላ ሺፋኡክ፣ ሺፋአን ላዩጋዲሩ ሰቀማ"» ትርጉሙም "የሰዎች ጌታ የሆንከው ሆይ! በሽታውን አስወግድ። አንተ ፈዋሽ ነህና ፈውሰው። በሽታን የማያስቀር ከሆነው ከአንተ ፈውስ በቀርም ሌላ ፈውስ የለም።" ማለት ነው።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2191]
ነቢዩ(የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሽተኛን የጠየቁ ጊዜ እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጉለት ነበር: አላህ ሆይ! (አዝሂብ) አስወግድ (አልባስ) የበሽታውን ሀይለኝነት (ረብበ ናስ) የሰዎች ፈጣሪና ተንከባካቢ የሆንከው! (ወሽፊ) ይህን በሽተኛ ፈውሰው (አንተ ሻፊ) ጥራት ይገባህና "አሽ‐ሻፊ" (ሁሉንም ፈዋሽ) በሚለው ስምህ ወዳንተ እቃረባለሁ። (ላሺፋአ) ህመምተኛ ላጋጠመው በሽታ ፈውስ የለም (ኢላ ሺፋኡክ) ከአንተ ፈውስ በቀር። (ሺፋአን) አጠቃላይ ፈውስን ስጠው (ላዩጋዲሩ) የማይተውና የማያስቀር የሆነን (ሰቀማ) ሌላን በሽታንም።