+ -

عن سعد بن أبي وقاص رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«إِنَّ اللهَ يُحِبُّ الْعَبْدَ التَّقِيَّ الْغَنِيَّ الْخَفِيَّ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2965]
المزيــد ...

ከሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህን መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
'አላህ ጥንቁቅ፣ (ከሰዎች) የተብቃቃና ድብቅ የሆነን ባሪያ ይወዳል።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2965]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ አንዳንድ ባሮቹን እንደሚወድ ገለፁ።
ከነርሱም መካከል ፈሪሃ አላህ የሆነ አንዱ ነው። እርሱም:- የአላህን ትእዛዛት የሚተገብርና ክልከላዎቹን የሚርቅ ነው።
ከሰዎች የተብቃቃንም ይወዳል። እርሱም:- በአላህ በመመካቱ የተነሳ ከሰዎች የተብቃቃና ከአላህ ውጪ ወደ ማንም የማይዞር ነው።
ድብቅንም ይወዳል። እርሱም:- ለጌታው ባሪያና የሚተናነስ፣ በሚጠቅመው ነገር ላይ የሚጠመድ፣ ማንም እርሱን ማወቁም ይሁን ስለርሱ በሙገሳና ውዳሴ ማውራቱን ከቁብ የማይቆጥር ሰው ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوكرانية الجورجية المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህ ባሮቹን እንዲወድ የሚያስፈርዱ አንዳንድ ባህሪያቶች መገለፃቸውን እንረዳለን። እነርሱም:- አላህን መፍራት፣ መተናነስና አላህ የሰጠንን ወደን መቀበል ነው።