+ -

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ رَضيَ اللهُ عنه:
أَنَّ جِبْرِيلَ أَتَى النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: يَا مُحَمَّدُ اشْتَكَيْتَ؟ فَقَالَ: «نَعَمْ» قَالَ: «بِاسْمِ اللهِ أَرْقِيكَ، مِنْ كُلِّ شَيْءٍ يُؤْذِيكَ، مِنْ شَرِّ كُلِّ نَفْسٍ أَوْ عَيْنِ حَاسِدٍ، اللهُ يَشْفِيكَ بِاسْمِ اللهِ أَرْقِيكَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2186]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
«ጂብሪል ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ መጣና እንዲህ አላቸው: "ሙሐመድ ሆይ! አመመህ እንዴ?" እርሳቸውም "አዎ" አሉ። እርሱም: "ቢስሚላሂ አርቂክ ሚን ኩሊ ሸይኢን ዩእዚክ ሚን ሸሪ ኩሊ ነፍሲን አው ዐይኒን ሓሲዲን አላሁ የሽፊክ ቢስሚላሂ አርቂክ" (ትርጉሙም: በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ። ከሁሉም ከሚያውክህ ነገር ፣ ከሁሉም ክፉ ነፍስ ወይም ምቀኛ አይን አላህ እንዲፈውስህ በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ።) አላቸው።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2186]

ትንታኔ

መልአኩ ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ወደ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በመምጣት ጠየቃቸው: "ሙሐመድ ሆይ! በህመም ተጠቃህን?" እርሳቸውም: "አዎ" አሉ። ጂብሪልም ነቢዩን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ በማለት ጥበቃ አደረገላቸው: "ቢስሚላሂ" በአላህ ስም ታግዤ "አርቂከ" እጠብቅሃለሁ። "ሚን ኩሊ ሸይኢን ዩእዚከ" ትንሽም ሆነ ትልቅ ከሚያውክህ ነገር ሁሉ እጠብቅሃለሁ። "ሚን ሸሪ ኩሊ ነፍሲን አው ዓይኒን ሓሲድ" ከሁሉም ክፉ ነፍስ ወይም ምቀኛ አይን እንዳያገኝህ እጠብቅሃለሁ። "አሏሁ የሽፊከ" አላህ ከሁሉም በሽታ እንዲፈውስህና እንዲጠብቅህ "ቢስሚላሂ አርቂከ" በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ። ("ቢስሚላሂ አርቂክ" የሚለውን) ሁለቴ የደጋገመውና በርሱ ጀምሮ በርሱ ያጠናቀቀው ከአላህ ውጪ ማንም እንደማይጠቅም ለመጠቆም ነው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በማማረርና በመበሳጨት መልኩ ሳይሆን ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ ለመግለፅ መታመምን መናገር ይፈቀዳል።
  2. ሩቅያህ (በማነብነብ መታከም) በሚከተሉት መስፈርቶች ይፈቀዳል። 1 - በቁርአን ወይም አላህን በማውሳትና ሸሪዓዊ በሆኑ ዱዓዎች መሆን ይገባዋል። 2 - በዐረብኛ ቋንቋ ወይም ሌላ ቋንቋም ቢሆን ትርጉሙ በሚታወቅ መሆን አለበት። 3 - ሩቃው በራሱ ምንም እንደማይፈይድ ማመን ይገባል። ሩቃው ከመዳኛ ሰበቦች መካከል አንዱ ሰበብ ብቻ ነው። በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በቀርም ምንም ተፅዕኖ አያሳድርም። 4 - ከሺርክ ወይም ከሐራም ወይም ከቢድዓ ወይም ወደነዚህ ከሚያደርሱ ነገሮች የራቀ መሆን አለበት።
  3. የሰው ዓይን እንደሚጎዳ መረጋገጡን እንመለከታለን። የሰው ዓይን ጎጂነቱ እውነት ነው። ለሰው ዓይን ህመም በሩቃ መታከም ተገቢ ነው።
  4. ሐዲሡ ላይ በተጠቀሰው የሩቃ ሕክምና መጠቀም ተወዳጅ እንደሆነ እንረዳለን።
  5. ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንደማንኛውም ሰው ናቸው። ሌሎች የሚያጋጥማቸው በሽታዎች እርሳቸውንም ያጋጥማቸዋል።
  6. አላህ ለነቢዩ ያለውን ጥበቃና እንክብካቤ፣ ለዚህም ጥበቃ መልአክቶቹን እንደመደበላቸው እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ተጨማሪ