عَنْ عُثْمَانَ بْنِ أَبِي الْعَاصِ الثَّقَفِيِّ رضي الله عنه أَنَّهُ شَكَا إِلَى رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَجَعًا يَجِدُهُ فِي جَسَدِهِ مُنْذُ أَسْلَمَ، فَقَالَ لَهُ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«ضَعْ يَدَكَ عَلَى الَّذِي تَأَلَّمَ مِنْ جَسَدِكَ، وَقُلْ بِاسْمِ اللهِ ثَلَاثًا، وَقُلْ سَبْعَ مَرَّاتٍ أَعُوذُ بِاللهِ وَقُدْرَتِهِ مِنْ شَرِّ مَا أَجِدُ وَأُحَاذِرُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2202]
المزيــد ...
ከዑሥማን ቢን አቢልዓስ አሥሠቀፊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ ከሰለመ ጊዜ ጀምሮ ሰውነቱ ውስጥ ስለሚሰማው ህመም ለአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አማከረ። የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለርሱ እንዲህ አሉት:
«እጅህን የሚያምህ ሰውነት ላይ አድርግና ሶስት ጊዜ "ቢስሚላህ" በል። ሰባት ጊዜ ደግሞ "አዑዙ ቢላሂ ወቁድረቲሂ ሚንሸሪ ማአጂዱ ወኡሓዚሩ" በል።» አሉት።" ትርጉሙም "ከሚሰማኝ ህመምና ከምፈራው አደጋ ክፋት በአላህና በችሎታው እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2202]
ዑሥማን ቢን አቢልዓስን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሊገድለው የቀረበ የሆነ በሽታ አጋጥሞት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሊጠይቁት መጡ። አላህ ያረፈበትን በሽታ እንዲያስወግድለት የሚያደርግ ዱዓንም አስተማሩት። ይሀውም የሚያመው ስፍራ ላይ እጁን በማድረግ ሶስት ጊዜ (ቢስሚላህ) ማለት ቀጥሎም ሰባት ጊዜ ይህንን ማለት (አዑዙ) እጠጋለሁ፣ እጠበቃለሁ (ከሚሰማኝ ክፋት በአላህና በችሎታው) አሁን ላይ ከሚያመኝ ህመም ማለት ነው። (ከምፈራው) ለወደፊት ከሚያገኘኝና ከምፈራው ሀዘንና ፍርሃት ወይም ይህ በሽታ ከመቀጠሉና ህመሙ በሰውነቴ ውስጥ ከመሰራጨቱ በአላህ እጠበቃለሁ ማለት ነው።