عن عقبة بن عامر رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«أَحَقُّ الشُّرُوطِ أَنْ تُوفُوا بِهِ مَا اسْتَحْلَلْتُمْ بِهِ الْفُرُوجَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2721]
المزيــد ...
ከዑቅበህ ቢን ዓሚር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
'ልታሟሉት ከሚገቡ መስፈርቶች ሁሉ ልታሟሉት እጅግ የተገባው ብልትን ሐላል ያደረጋቹበትን መስፈርት ነው።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2721]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መሙላቱ እጅግ የተገባው መስፈርት በሴት መጠቀምን ሐላል ለማድረግ ሰበብ የሆነውን መስፈርት መሆኑን እየነገሩን ነው። ይህም ሚስት በጋብቻው ውል ወቅት የምታስቀምጣቸው የተፈቀዱ መስፈርቶች ናቸው።