عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ رَضيَ اللهُ عنهُما:
أَنَّ أُمَّهُ بِنْتَ رَوَاحَةَ سَأَلَتْ أَبَاهُ بَعْضَ الْمَوْهِبَةِ مِنْ مَالِهِ لِابْنِهَا، فَالْتَوَى بِهَا سَنَةً ثُمَّ بَدَا لَهُ، فَقَالَتْ: لَا أَرْضَى حَتَّى تُشْهِدَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَلَى مَا وَهَبْتَ لِابْنِي، فَأَخَذَ أَبِي بِيَدِي وَأَنَا يَوْمَئِذٍ غُلَامٌ، فَأَتَى رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: يَا رَسُولَ اللهِ، إِنَّ أُمَّ هَذَا بِنْتَ رَوَاحَةَ أَعْجَبَهَا أَنْ أُشْهِدَكَ عَلَى الَّذِي وَهَبْتُ لِابْنِهَا، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «يَا بَشِيرُ، أَلَكَ وَلَدٌ سِوَى هَذَا؟» قَالَ: نَعَمْ، فَقَالَ: «أَكُلَّهُمْ وَهَبْتَ لَهُ مِثْلَ هَذَا؟» قَالَ: لَا، قَالَ: «فَلَا تُشْهِدْنِي إِذن، فَإِنِّي لَا أَشْهَدُ عَلَى جَوْرٍ»، ولِمُسْلِمٍ: «فَأَشْهِدْ عَلَى هَذَا غَيْرِي».
[صحيح] - [متفق عليه، وله ألفاظ عديدة] - [صحيح مسلم: 1623]
المزيــد ...
ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዺየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
«የኑዕማን እናት ቢንት ረዋሓ ለልጇ ኑዕማን ከገንዘቡ የተወሰነ ስጦታ እንዲሰጠው አባቱን ጠየቀችው። አንድ ዓመት ከዘገየ በኋላ ስጦታውን መስጠቱ ላይ ተስማማ። እርሷም "ለልጄ በምትሰጠው ስጦታ የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እስክታስመሰክር ድረስ አልደሰትም።" አለች። እኔም ህፃን ነበርኩኝና አባቴ እጄን ይዞ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ መጣ። እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዚህ ልጅ እናቱ ቢንት ረዋሓ ለልጄ በምሰጠው ስጦታ ምስክር እንዳደርጎት ወደደች።" አለ። የአላህም መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "በሺር ሆይ! ከዚህ ልጅ ውጪ ሌላ ልጅ አለህን?" አሉ። እርሱም "አዎን" አለኝ አለ። እርሳቸውም "ለዚህ ልጅ የምትሰጠውን ስጦታ አምሳያ ለሁሉም ሰጥተሃልን?" አሉት። እርሱም "አይ" አለ። እርሳቸውም "እንዲያ ከሆነ እኔን አታስመስክረኝ! እኔ በበደል ላይ አልመሰክርም።" አሉ። በሙስሊም ዘገባ ደሞ "በዚህ ጉዳይ ከኔ ውጪ የሆነን አስመስክር" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1623]
ኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እናቱ ዐምረህ ቢንት ረዋሓ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - አባቱ ከገንዘቡ የተወሰነ ስጦታን ለልጇ እንዲሰጥ እንደጠየቀችው ተናገረ። ስለከበደው አንድ አመት ካዘገየ በኃላ ፍላጎቷን በማሟላት ለልጁ ኑዕማን ስጦታ መስጠት ታየው። እርሷም እንዲህ አለች: "ለልጄ በምትሰጠው ስጦታ የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እስክታስመሰክር ድረስ አልወድም።" እኔም በዛን ግዜ ህፃን ነበርኩኝ። አባቴ እጄን ይዞ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዚህ ልጅ እናት ቢንት ረዋሓ ለልጇ በምሰጠው ስጦታ እርሶን ማስመስከሬን ወደደች።" እርሳቸውም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "በሺር ሆይ! ከዚህ ልጅ ውጪ ሌላ ልጅ አለህን?" እርሱም "አዎን" አለ። እርሳቸውም "ይህን የመሰለ ስጦታ ለሁሉም ልጆችህ ሰጥተሃልን?" አሉት። እርሱም "አይ" አለ። እርሳቸውም "እንዲህ ከሆነ አታስመስክረኝ። እኔ በግፍና በበደል ላይ አልመሰክርም።" አሉ። ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ ደግሞ እርሱን በመውቀስ መልኩ "ይልቁን በዚህ በደልህ ከኔ ውጪ ሌላን አስመስክር።" አሉት።