+ -

عَنِ ابْنِ عُمَرَ رَضيَ اللهُ عنهما قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنَّ أَحَبَّ أَسْمَائِكُمْ إِلَى اللهِ عَبْدُ اللهِ وَعَبْدُ الرَّحْمَنِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2132]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ከስሞቻችሁ መካከል አላህ ዘንድ ተወዳጁ ስም ዐብዱላህና ዐብዱረሕማን ናቸው።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2132]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከወንድ ስሞች መካከል አላህ ዘንድ ተወዳጁ ስም ዐብዱላህና ዓብዱራሕማን ተብሎ መጠራት እንደሆነ ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ቁርጡቢይ እንዲህ ብለዋል: " እንደ ዐብዱረሒም፣ ዐብዱልመሊክና ዐብዱሶመድ የመሰሉ ከነዚህ ሁለት ስሞች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ስሞችም ወደነርሱ ይጠጋሉ። አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑበት ምክንያትም የአላህን ግድ የሆነን ባህሪ ጌትነትን፣ የሰው ልጅንም ግድ የሆነን ባህሪ ባሪያነትን ስለያዙ ነው። ቀጥሎም ባሪያው ወደ ጌታው ባርነቱ እውነተኛ በሆነ መልኩ ስለተጠጋና እያንዳንዱ ስሞች በተናጠል እውነታውን ስላረጋገጡ ነው። በዚህ ጥምር ቃልም እያንዳንዱ ስሞች ስለላቁ ይህን ደረጃ አገኙ።" ሌሎች ዑለማዎች ደግሞ እንዲህ ብለዋል: "በነዚህ ሁለት ስሞች ብቻ የተገደቡበት ጥበብ ቁርአን ውስጥ ባሪያነት ወደ አላህ ስም የተጠጋው ወደነዚህ ሁለት ስሞች ብቻ ስለሆነ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል {እነሆም የአላህ ባሪያ (ዐብዱላህ) የሚጠራው ሆኖ በተነሳ ጊዜ} በሌላ አንቀፅም {የአርረሕማን ባሮች} ይህንንም {… አላህን ጥሩ ወይም አርረሕማንን ጥሩ… } የሚለው የአላህ ንግግር ያጠናክረዋል።"
ትርጉም: እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ሲንሃላዊ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ