+ -

عَن أَبي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ قَالَ: رَضِيتُ بِاللَّهِ رَبًّا، وَبِالْإِسْلَامِ دِينًا، وَبِمُحَمَّدٍ رَسُولًا، وَجَبَتْ لَهُ الْجَنَّةُ».

[صحيح] - [رواه أبو داود] - [سنن أبي داود: 1529]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"በአላህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ መልክተኝነት ወድጃለሁ ያለ ሰው ጀነት ለርሱ ፀንታለታለች።"

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 1529]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) (ረዲቱ ቢላሂ ረብበን) በአላህ አምላክነት፣ ተንከባካቢነት፣ ንጉስነት፣ አለቃነት፣ አስተካካይነት ወድጃለሁ፤ (ወቢልኢስላሚ) በእስልምና በሁሉም ትእዛዛዊና ክልከላዊ ህግጋቶቹ (ዲነን) መንገድነት፣ ሃይማኖትነትና እምነትነት ወድጃለሁ፤ (ወቢሙሐመደን ረሱላ) በሙሐመድ ነቢይነት፣ እርሳቸው በተላኩበትና ወደኛ ባደረሱት ነገር ሁሉ ወድጃለሁ ያለ ሰው ጀነት ለርሱ እንደፀናችለት ተናገሩ።

ትርጉም: ኢንዶኔዥያኛ ቬትናማዊ ሃውሳ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ይህን ዱዓ በማለት ላይ መነሳሳቱንና ይህንን ዱዓ ማለትን ተከትሎ የሚገኘው ምንዳ መገለፁን እንረዳለን።
  2. በአላህ ጌትነት መውደድ ሲባል ሰውዬው ከአላህ ሱብሓነሁ ውጪ ያለን አለመገዛቱንም ያካትታል።
  3. በሙሐመድ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ነቢይነትና መልክተኝነት መውደድም ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መታዘዝና ለሱናቸው ተገዢ መሆንን ያካትታል።
  4. በእስልምና ሃይማኖትነት መውደድ ሲባል አላህ ለባሮቹ የመረጠውን መውደድ ማለት ነው።
  5. በሌላ ዘገባ እንደመጣው አዛን በሚባልበት ጊዜ ሁለቱን የምስክርነት ቃላት ካለ በኋላ ይህን ዱዓ ማለት ይወደዳል።
  6. በሌላ ሐዲሥ እንደመጣው ደሞ ይህን ዱዓ ንጋትና ምሽት ላይ ማለትም ይወደዳል።