عن ابن عمر رضي الله عنهما:
أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ نَهَى عَنِ الْقَزَعِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5921]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው:
"የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከልክለዋል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5921]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የጭንቅላት ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከለከሉ።
ክልከላው ልጅም አዋቂም ወንዶችን የሚያጠቃልል ነው። ሴት ግን የጭንቅላት ፀጉሯን መላጨት አይፈቀድላትም።