عن أبي هريرة رضي الله عنه قال:
لعن رسول الله صلى الله عليه وسلم الرجل يلبس لِبْسَةَ المرأة، والمرأة تلبس لِبْسَةَ الرجل.
[صحيح] - [رواه النسائي في الكبرى وابن ماجه بمعناه وأحمد] - [السنن الكبرى للنسائي: 9209]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሴት ልጅ አለባበስን የሚለብስን ወንድና የወንድ ልጅ አለባበስን የምትለብስ ሴትን ረገሙ።"
[ሶሒሕ ነው።] - - [አስሱነኑል ኩብራ ነሳኢ - 9209]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በአኳኋኑም ይሁን በቀለሙም፣ በአይነቱም ይሁን በአለባበስ መንገዱም፣ በመዋቢያነቱ (ማስጌጫዎች)ና በመሳሰሉ መንገዶች ሴት ልጅ የተለየችበት በሆነ ልብስ የሚመሳሰል ወንድ ላይ ከአላህ እዝነት እንዲባረርና እንዲርቅ ዱዓእ አድርገዋል። ወይም ልክ እንደዚሁ ወንድ ልጅ በተለየበት ልብስ የምትመሳሰል ሴት ልጅ ከአላህ እዝነት እንዲባረሩና እንዲርቁ ዱዓ አደረጉ። ይህም ከትላልቅ ወንጀሎች የሚመደብ ከባድ ወንጀል ነው።