عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَا أَسْفَلَ مِنَ الكَعْبَيْنِ مِنَ الإِزَارِ فَفِي النَّارِ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 5787]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ሽርጡን ከቁርጭሚቶች ዝቅ ያደረገ እሳት ውስጥ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5787]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ወንዶች ከወገባቸው በታች ያለ አካላቸውን የሚሸፍነውን ልብስ ወይም ሱሪያቸውን ወይም ከዛም ውጪ የሆነውን ልብስ ከቁርጭምጭሚታቸው በታች ዝቅ ከማድረግ አስጠነቀቋቸው። ሽርጡን ከቁርጭምጭሚቱ በታች ዝቅ ያደረገው ሰውዬም ለሰራው ስራ ቅጣት ይሆነው ዘንድ እግሩ እሳት ውስጥ ይሆናል።