عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما قال:
لعن النبي صلى الله عليه وسلم الوَاصِلَةَ والمُسْتَوْصِلَةَ، والوَاشِمَةَ والمُسْتَوشِمَةَ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5947]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ፀጉር የምትቀጥልን፣ የምታስቀጥልን፣ የምትነቅስንና የምታስነቅስን ረግመዋል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5947]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አራት አካላቶች ላይ እርግማንንና ከአላህ እዝነት መራቅን ዱዓ አደረጉባቸው። የመጀመሪያው: የራሷን ወይም የሌላን ሰው ፀጉር በሌላ ፀጉር የምትቀጥል ናት። ሁለተኛው: ሌላ ሰው ፀጉሯን በሌላ ፀጉር እንዲቀጥልላት የምትጠይቅና የምታስቀጥል ናት። ሶስተኛው: ማማርና ውበትን በመፈለግ ፊትን ወይም እጅን ወይም ደረትን የመሰሉ የሰውነት አካላቶችን በመርፌ በመጠቅጠቅ ምልክቱ ሰማያዊ ወይም አረንጓዴ እስኪሆን ድረስ ኩልን ወይም የመሳሰሉትን ቦታው ላይ እየቀባች የምትነቅስ ናት። አራተኛ: ንቅሳት እንዲፈፀምባት የምትፈልግ ናት። እነዚህ ተግባራት ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል የሚመደቡ ናቸው።