عَنْ مُعَاوِيَةَ الْقُشَيْرِيِّ رضي الله عنه قَالَ:
قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، مَا حَقُّ زَوْجَةِ أَحَدِنَا عَلَيْهِ؟، قَالَ: «أَنْ تُطْعِمَهَا إِذَا طَعِمْتَ، وَتَكْسُوَهَا إِذَا اكْتَسَيْتَ، أَوِ اكْتَسَبْتَ، وَلَا تَضْرِبِ الْوَجْهَ، وَلَا تُقَبِّحْ، وَلَا تَهْجُرْ إِلَّا فِي الْبَيْتِ»
[حسن] - [رواه أبو داود وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 2142]
المزيــد ...
ከሙዓዊያ አልቁሸይሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሚስታችን እኛ ላይ ያላት ሐቅ ምንድን ነው? አልኩኝ። እርሳቸውም "ስትበላ ልታበላት፤ የለበስክ ወይም የሰራህ ጊዜ ልታለብሳት፤ ፊቷን ላትመታ፤ ላታጥላላት፤ ከቤት ውጪ ባለ ቦታ ላታኮርፋት ነው።" በማለት መለሱልኝ።»
[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 2142]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባል ላይ ያለበት የሚስት ሐቅ ምንድን ነው? ተብለው ተጠየቁ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የተወሰኑ ጉዳዮችን ጠቀሱ። ከነርሱም መካከል:
የመጀመሪያው: እርሷን ትተህ ነፍስህን በምግብ ላትነጥል ነው። ይልቁንም በበላህና በተመገብክ ቁጥር እርሷንም አብላት።
ሁለተኛው: ነፍስህን በልብስ ላትነጥል ነው። ይልቁንም የለበስክ ወይም ሰርተህ መግዛት የቻልክ ጊዜ አልብሳት።
ሶስተኛው: ለምክንያትና አስፈላጊ ሲሆን ካልሆነ በቀር ላትመታት፤ ስርዓት ለማስያዝ ወይም አንዳንድ ግዴታዎችን ስለተወች ሊመታት ከፈለገ የማያቆስል ምት ሊመታት፤ ፊቷንም ላይመታት ነው። ይህም ፊት ታላቁ፣ ግልፅ የሆነ፣ የተከበሩና ስስ የሰውነት ክፍሎችን ያካተተ የሰውነት ክፍል ስለሆነ ነው።
አራተኛው: አትስደባት ወይም አላህ ፊትሽን አስቀያሚ ያርገው አትበል። ፊቷን ወይም አንድ የሰውነት አካሏን በአስቀያሚነት አትግለፀው። የሰዎችን ፊት እና አካል የቀረፀው፣ የሁሉንም ነገር ፍጥረትም ያሳመረው አላህ ነውና። አፈጣጠርን መተቸት አላህ ይጠብቀንና ፈጣሪን ወደ መተቸት ነው የሚመለሰው።
አምስተኛው: መኝታ ስፍራ ላይ ካልሆነ በቀር አታኩርፋት። እርሷን ትተህ ሌላ ቤት እንዳትቀይር፣ እርሷንም ወደ ሌላ ቤት አትሸኛት። ምናልባት ይህ ባልና ሚስት ሲኮራረፉ መከሰቱ የተለመደ ቢሆንም ግን ልክ አይደለም።