+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ كَانَتْ لَهُ امْرَأَتَانِ فَمَالَ إِلَى إِحْدَاهُمَا، جَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَشِقُّهُ مَائِلٌ».

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 2133]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"ለርሱ ሁለት ሚስቶች ኑረውት ወደ አንዳቸው የተዘነበለ የትንሳኤ ቀን ጎኑ የተንሻፈፈ ሆኖ ይመጣል።"

[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን አቡዳውድ - 2133]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለርሱ ከአንድ በላይ ሚስቶች ኑረውት በመካከላቸው በሚያወጣው ወጪ፣ በቤት፣ በልብስና በማደር በሚስቶቹ መካከል የቻለውን ፍትህ ያላሰፈነ ሰው የትንሳኤ ቀን የሚቀጣው ግማሽ ሰውነቱ እንዲያንሻፍፍ በመደረግ እንደሆነ ተናገሩ። መንሻፈፉም ከሚስቶቹ ጋር በነበረው መስተጋብር እንደተዘነበለው ለሰራው በደል ቅጣት ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አንድ ወንድ በሁለት ወይም ከዛ በላይ በሆኑ ሚስቶቹ መካከል ማከፋፈል ግዴታው እንደሆነና በሚችለው ቀለብ፣ በአዳር፣ በመልካም መስተጋብርና በመሳሰሉት ከአንዷ ወደ አንዷ መዘንበሉም ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
  2. አንድ ባል በሚችለው በሆነ በማከፋፈልና በመሳሰሉት እኩኩል ማድረግ አለበት። እንደፍቅርና ቀልባዊ መዘንበል የመሰለ የማይችለው በሆነ ነገር ሐዲሡ ውስጥ አይካተትም። {በሴቶች መካከል ምንም እንኳ ብትጓጉ (በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም።} [አንኒሳእ: 129] በሚለው የአላህ ንግግር የተፈለገውም ይህ ነው።
  3. ምንዳ የሚመነዳው በስራው አይነት ነው። ወንዱ በዱንያ ውስጥ ከአንዷ ሚስቱ ወደ ሌላኛዋ ስለተዘነበለ የትንሳኤ ቀንም አንዱ ጎኑ ከሌላኛው የተዘነበለ ሆኖ ይመጣል።
  4. የባሮች ሐቅ የላቀ መሆኑንና ይቅር የማይባል ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን። ምክንያቱም በስስትና በፍርድ ላይ የተመሰረተ ፍርድ ነውና የሚፈረደው።
  5. በሚስቶች መካከል በፍትህ አለማኖርን ከፈራ የዲን ጉድለት ላይ እንዳይወድቅ በአንድ ሚስት ብቻ መታቀብ እንደሚወደድ እንረዳለን። አላህ እንዲህ ብሏል: {አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ያዙ።} [አንኒሳእ:3]