+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ اللَّهَ تَجَاوَزَ عَنْ أُمَّتِي مَا حَدَّثَتْ بِهِ أَنْفُسَهَا، مَا لَمْ تَعْمَلْ أَوْ تَتَكَلَّمْ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5269]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ዲዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"አላህ ከኡመቴ በውስጣቸው የሚናገሩትን ነገር እስካልሰሩት ወይም እስካልተናገሩት ድረስ ይቅር ብሏቸዋል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5269]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ ወንጀልነቱን ስላነሳና ይቅር ስላለ አንድ ሙስሊም በውስጡ አስቦ ለተወው መጥፎ ነገር እስካልሰራበት ወይም እስካልተናገረው ድረስ እንደማይያዝበት ተናገሩ። የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ኡመት በአይምሯቸው በሚገኝ፣ ልባቸው ላይ ሳይረጋጋና ሳይፀናበት ውስጣቸው ላይ በመጣ መጥፎ ነገር አይያዙም። እንደኩራት፣ መንጠባረርና ንፍቅና ቀልቡ ላይ ከፀናበት፣ በአካሉ ከተገበረ ወይም በምላሱ ከተናገረ ግን ይያዝበታል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህ ተባረከ ወተዓላ በነፍስ ላይ የምትመጣንና ሰውዬው በውስጡ የሚናገራትንና ውል የምትልበትን አስተሳሰብና ሹክሹክታ ይቅር ብሏልም አልፏልም።
  2. አንድ ሰው ሚስቱን መፍታት ቢያስብና በውስጡ ውል ቢልበትም ነገር ግን ካልተናገረና ካልፃፈው ፍቺ ተደርጎ አይቆጠርበትም።
  3. በውስጥ የሚወራ ወሬ ምንም ያህል ቢገዝፍ በውስጡ እስካልፀና፣ በርሱ እስካልሰራ ወይም እስካልተናገረ ድረስ አይያዝበትም።
  4. የሙሐመድ ኡመት (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከኛ በፊት ከነበሩት ህዝቦች በተቃራኒ ከራሳቸው ጋር በውስጥ በማውራታቸው ባለመያዝ የተለዩ መሆናቸው ደረጃቸው የላቀ መሆኑን ያስረዳናል።
ተጨማሪ