+ -

عن علي رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«رُفِعَ الْقَلَمُ عن ثلاثة: عن النائم حتى يَسْتَيْقِظَ، وعن الصبي حتى يَحْتَلِمَ، وعن المجنون حتى يَعْقِلَ».

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي في الكبرى وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 4403]
المزيــد ...

ከዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ከሶስት ዓይነት አካላት ላይ ብእር ተነስቷል። የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ፤ ህፃን ልጅ አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ እና እብድ ጤነኛ እስኪሆን ድረስ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል። - ቲርሚዚ ዘግበውታል። - አቡዳውድ ዘግበውታል። - አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 4403]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከነዚህ ሶስት አካላት በቀር የግዴታ ነገሮች ተጠያቂነት ለአደም ልጆች ሁሉ የማይቀር እንደሆነ ተናገሩ።
ጨቅላ ህፃን ልጅ እስኪተልቅና አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ፤
አይምሮውን ያጣ እብድ አይምሮው ወደርሱ እስኪመለስለት ድረስ፤
እንቅልፉን የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ ናቸው።
ከነዚህ አካላት ተጠያቂነት ተነስቷል። ወንጀል ቢሰሩ በነርሱ ላይ አይፃፍም። ነገር ግን ከእብድና የተኛ ሰው ውጪ ለትንሽ ህፃን ልጅ መልካም ስራ ከሰራ ይፃፍለታል። ይህም እብድና የተኛ ሰው አይምሮዋቸው ስለተወገደ አምልኮን አስተካክለው የሚፈፅሙ አካላት ስላልሆኑ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሰው ልጅ ተጠያቂነት የሚነሳለት ወይ ግዴታውን ከመፈፀም መንቃት እንዳይችል ባደረገው እንቅልፍ ምክንያት ነው፤ ወይም ከተጠያቂነት እድሜ በማነሱና ልጅ በመሆኑ ምክንያት ነው ፤ ወይም የአይምሮው ተግባር የተምታታበት እብድ በመሆኑ ወይም ወደ እብደት የተጠጋ ስካር ላይ በመሆኑ ምክንያት ነው። ትክክለኛ መለየትንና መረዳት ያልቻለ ሰውና በነዚህ ሶስት ምክንያቶች ሳቢያ ለተጠያቂነት ብቁ ያልሆነ ሰው አላህ ተባረከ ወተዓላ በፍትሃዊነቱ፣ በቻይነቱና ቸርነቱ በአላህ ሐቅ ላይ ከሚያጓድለው ወይም ወሰን ከሚያልፈው ነገር ተጠያቂነቱን አንስቶለታል።
  2. በነርሱ ላይ ወንጀል አለመፃፉ አንዳንድ ዱንያዊ ፍርዶች ይመለከታቸዋል ከሚለው ጋር አይጣረስም። ለምሳሌ እብድ ቢገል የመገደልና ጉማ የመክፈል ግዴታ የለበትም። በወራሽ ቤተሰቦቹ (የርሱ "ዓቂላ" በሆኑት) ላይ ግን ጉማ የመክፈል ግዴታ አለባቸው።
  3. ለአቅመ አዳምነት መድረስ ሶስት ምልክቶች አሉት: በህልም ወይም በሌላ ምክንያት የዘር ፈሳሽ ማፍሰስ ወይም የብልት አካባቢ ፀጉር በማብቀል ወይም አስራ አምስት አመት በመሙላት ነው። ሴት ከሆነች አራተኛ ምልክት አላት፤ እርሱም የወር አበባ ማየት ነው።
  4. ሱብኪ እንዲህ ብለዋል: ጨቅላ በማለት የተፈለገው ህፃን ልጅ ማለት ነው። ሌሎች ዑለሞች ደግሞ: ልጅ እናቱ ሆድ ውስጥ እያለ ፅንስ ይባላል። ሲወለድ ጨቅላ ሲጠነክር ጀምሮ እስከ ሰባት አመቱ ደግሞ ህፃን ይባላል። ከዚያም እስከ አስር አመቱ ለምድ አዙር ይባላል። ከዚያም እስከ አስራ አምስት አመቱ ደግሞ የደረሰ ይባላል። በነዚህ ሁሉ አመታት ውስጥ ባለው እርከን ህፃን ልጅ ከመባል አይወገድም ብለዋል። ይህንም የተነተኑት ሱዩጢይ ናቸው።