عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لاَ يُصَلِّي أَحَدُكُمْ فِي الثَّوْبِ الوَاحِدِ لَيْسَ عَلَى عَاتِقَيْهِ شَيْءٌ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 359]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"አንዳችሁ ትከሻዎቹ ላይ አንዳችም ነገር የሌለ ሆኖ በአንድ ልብስ ብቻ አይስገድ።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 359]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአንድ ልብስ የሰገደ ሰው ሁለት ትከሻዎቹን (ከአንገቱ እስከ ማጅራቱ ያለውን) አንዳች መሸፈኛ በነርሱ ላይ ሳያደርግ ራቁት አድርጎ መስገዱን ከለከሉ። ሁለቱ ትከሻዎች ሀፍረተ ገላ ባይሆኑም እንኳ ሀፍረተ ገላ ሲሸፈኑ አብሮ ለመሸፈን የተመቹ ናቸውና። በሶላት ውስጥ አላህ ፊት ሲቆምም አላህን ለማላቅና ለማክበር የቀረበ ነው።