عن أبي مَرْثَدٍ الغَنَوِيّ رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«لَا تَجْلِسُوا عَلَى الْقُبُورِ، وَلَا تُصَلُّوا إِلَيْهَا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 972]
المزيــد ...
ከአቡ መርሠድ አልጘነዊይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 972]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መቃብሮች ላይ ከመቀመጥ ከለከሉ።
ይህም ወደ መቃብሮች ከመስገድ እንደከለከሉት ነው። ቀብሩ ወደ ሰጋጁ ቂብላ አቅጣጫ መሆኑን ይመስል ማለት ነው። ይህም የተከለከለው ወደ ሺርክ ከሚያዳርሱ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ነው።