عن أبي أمامة الباهلي رضي الله عنه قال: سمعتُ رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«اقرؤوا القرآنَ فإنَّه يأتي يوم القيامة شَفِيعًا لأصحابه، اقرؤوا الزَّهرَاوَين البقرةَ وسورةَ آل عِمران، فإنهما تأتِيان يوم القيامة كأنهما غَمَامَتان، أو كأنهما غَيَايَتانِ، أو كأنهما فِرْقانِ من طَيْر صَوافٍّ، تُحاجَّان عن أصحابهما، اقرؤوا سورة البقرة، فإن أخذها بَرَكة، وتركها حَسْرة، ولا تستطيعها البَطَلَة».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 804]
المزيــد ...
ከአቡ ኡማመተል ባሂሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
"ቁርአንን ቅሩ! እርሱ የትንሳኤ ቀን ለባለቤቶቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣል። ሁለቱን አብሪ የሆኑ ምዕራፎች ሱረቱል በቀራንና አሉ ዒምራንን ቅሩ። እነርሱ የትንሳኤ ቀን ልክ ደመና ወይም ጥላ መስለው ወይም ተጠባብቀው ረድፍ የሰሩ የወፎች ሁለት መንጋ መስለው ይመጣሉ። ለባለቤቶቻቸውም ይሟገታሉ። የበቀራን ምዕራፍ ቅሩ! እርሷን መያዝ በረከት ነው። እርሷን መተው ደግሞ የሚያስቆጭ ነው። ደጋሚዎችም አይችሏትም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 804]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቁርአንን አዘውትሮ በመቅራት ላይ አነሳሱ። ቁርአን የትንሳኤ ቀን ለሚያነቡትና በርሱ ለሚተገብሩ ሰዎች ያማልዳል። ቀጥለውም የበቀራንና የአሉ ዒምራንን ምዕራፎች በማንበብ ላይ ጠንከር አድርገው አነሳሱ። ስለሚመሩና ስለሚያበሩም አብሪዎች ብለው ሰየሟቸው። እነርሱን የማንበብ፣ ትርጉማቸውን የማስተንተንና ውስጣቸው ባለው የመተግበር ምንዳና አጅርም የትንሳኤ ቀን እንደ ሁለት ደመና ወይም ሌላ ጥላ ወይም እርስ በርስ ተጠባብቀው ክንፋቸውን እንደዘረጉ ሁለት የበራሪ መንጋ ተመስለው ባለቤቶቻቸውን አስጠልለው የሚከላከሉለት መሆናቸውን ተናገሩ። አስከትለውም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የበቀራን ምዕራፍ አዘውትሮ በመቅራት፣ ትርጉሙን በማስተንተንና ውስጡ ባለው በመስራት ላይ አጠንክረው አነሳሱ። ይህም ውስጡ በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ትልቅ በረከትና ጥቅም ስላለው እና ይህንን መተውም የትንሳኤ ቀን ቁጭትና ፀፀት ይዞ ስለሚመጣ ነው። ከዚህ ምዕራፍ ደረጃዎች መካከልም ደጋሚዎች ይህንን ምዕራፍ የሚቀራን ሰው ሊጎዱ አለመቻላቸው ተጠቃሽ ነው።