عَن أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَا بَالُ أَقْوَامٍ يَرْفَعُونَ أَبْصَارَهُمْ إِلَى السَّمَاءِ فِي صَلاَتِهِمْ»، فَاشْتَدَّ قَوْلُهُ فِي ذَلِكَ، حَتَّى قَالَ: «لَيَنْتَهُنَّ عَنْ ذَلِكَ أَوْ لَتُخْطَفَنَّ أَبْصَارُهُمْ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 750]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ሰዎች ሶላታቸው ውስጥ ሆነው ዓይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉት ምን ሆነው ነው!?" በዚህ ዙሪያም አጠንክረው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ "ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ ወይም አይናቸው ትነጠቃለች።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 750]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሶላት ውስጥ ሆነው ዱዓ ሲያደርጉም ይሁን ሌላ ድርጊት ሲያደርጉ አይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉ ሰዎችን አስጠነቀቁ። ቀጥለውም ይህንን በሚፈፅሙ ሰዎች ላይ ማስጠንቀቂያቸውንና ዛቻቸውን አበረቱ። በማያውቁት መልኩ የማየትን ፀጋ በሚያጡበት ሁኔታ አይኖቻቸውን የመነጠቅና በፍጥነት የመጥፋት አደጋ እንደሚፈራለትም አሳሰቡ።