عن عَائِشَةَ رضيَ الله عنها قالت: إِنِّي سمعْتُ رسولَ الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«لَا صَلَاةَ بِحَضْرَةِ الطَّعَامِ، وَلَا هُوَ يُدَافِعُهُ الْأَخْبَثَانِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 560]
المزيــد ...

ከእናትችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦
"ምግብ ቀርቦ አልያም ሁለቱ ቆሻሻዎች እያጨናነቁት ሶላት የለም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 560]

ማብራሪያ

የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሰጋጅ ነፍስ የሚጓጓውና ልቡ የተንጠለጠለበት ምግብ ቀርቦ መስገድን ከለከሉ።
ልክ እንደዚሁ በቆሻሻው ግፊት ስለሚጠመድም ሁለቱ ቆሻሾች እያጨናነቁት ከመስገድ ከለከሉ። (እነርሱም ሽንትና አይነ ምድር ናቸው።)

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. አንድ ሰጋጅ ወደ ሶላት ከመግባቱ በፊት ከሶላቱ የሚያዘናጋውን ነገር ባጠቃላይ ማራቅ ይገባዋል።
ትርጉሞችን አሳይ
ቋንቋ: الإنجليزية الأوردية الإسبانية ተጨማሪ (61)