عن أنس بن مالك رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ نَسِيَ صَلَاةً فَلْيُصَلِّ إِذَا ذَكَرَهَا، لَا كَفَّارَةَ لَهَا إِلَّا ذَلِكَ: {وَأَقِمِ الصَّلاةَ لِذِكْرِي} [طه: 14]».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 597]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"ሶላትን የረሳ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ይስገድ። ከዚህ በቀር ማካካሻ የለውም። {ሶላትንም (በርሷ) እኔን ለማስታወስ ስገድ።} [ጣሀ:14]
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 597]
የትኛውንም የግዴታ ሶላት ወቅቱ እስኪወጣ ድረስ መስገድን የረሳ ሰው ባስታወሰ ወቅት ቀዿእ ለማድረግ መፍጠን እንደሚገባው፤ አንድ ሙስሊም በወቅቱ መስገድን በመተዉ ለፈፀመው ወንጀልም ባስታወሰ ወቅት መስገዱ እንጂ ሌላ ምንም ማበሻና ማስማሪያ እንደሌለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ። አላህ በተከበረው መጽሐፉ እንዲህ ብሏል {ሶላትንም (በርሷ) እኔን ለማስታወስ ስገድ።} [ጣሀ:14] ማለትም የተረሳን ሶላት ባስታወስካት ወቅት ቀጥ አድርገህ ስገድ ማለትም ነው።