+ -

عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بنِ مسعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ:
ذُكِرَ عِنْدَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ رَجُلٌ نَامَ لَيْلَهُ حَتَّى أَصْبَحَ، قَالَ: «ذَاكَ رَجُلٌ بَالَ الشَّيْطَانُ فِي أُذُنَيْهِ، أَوْ قَالَ: فِي أُذُنِهِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3270]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋ ድረስ ምሽቱን የተኛ ሰውዬ ተወሳ። እርሳቸውም "ይህ ሸይጧን ጆሮዎቹ ውስጥ ወይም ጆሮው ውስጥ የሸናበት ሰው ነው።" አሉ።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3270]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋና ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ የተኛ፤ ግዴታ ሶላትን ለመስገድም ስላልተነሳ ሰውዬ ተወሳ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህ ሸይጧን ጆሮው ውስጥ የሸናበት ሰው ነው አሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية النيبالية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሌሊት ሶላት መቆምን መተው እንደሚጠላና ይህም በሸይጧን አማካይነት እንደሚሆን ተረድተናል።
  2. በርሱና አላህን በመታዘዝ መካከል እንቅፋት ለመሆን በሁሉም መንገድ ላይ የሰውን ልጅ ለመከልከል ከሚቀመጠው ሸይጧን መጠንቀቅ እንደሚገባ ተረድተናል።
  3. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: (ወደ ሶላት ያልቆመ) በሚለው የተፈለገው ማንኛውም የሶላት አይነትም ሊሆን ይችላል፤ ተለይቶ የታወቀን ሶላት ሊሆንም ይችላል፤ የለይል ሶላትም ሊሆን ይችላል፤ የግዴታ ሶላትም ሊሆን ይችላል።
  4. ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: «ቦታው ላይ ለመጥቀስ ከእንቅልፍ ጋር አብሮ የሚሄደው አካል አይን ከመሆኑም ጋር ጆሮን ለይተው የጠቀሱት የእንቅልፉን ክብደት ለመግለፅ ነው። መስሚያዎች መንቂያ አካላቶች ናቸውና። ሽንት የተለየበት ምክንያትም ደሞ ወደ ውስጥ ለመግባት ቀላልና ወደ ደም ስር ለመስረፅ ፈጣን ስለሆነ ነው። ይህም ከሆነ በኋላ ለሁሉም አካል መስነፍን ያወርሳል።»