+ -

«خَيْرُ يَوْمٍ طَلَعَتْ عَلَيْهِ الشَّمْسُ يَوْمُ الْجُمُعَةِ*، فِيهِ خُلِقَ آدَمُ، وَفِيهِ أُدْخِلَ الْجَنَّةَ، وَفِيهِ أُخْرِجَ مِنْهَا، وَلَا تَقُومُ السَّاعَةُ إِلَّا فِي يَوْمِ الْجُمُعَةِ».
[صحيح] - [رواه مسلم]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁመዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን ኣደም ተፈጠረ፣ በዚሁ ቀን ጀነት ገባ፣ በዚሁ ቀን ከርሷ ወጣ፣ ሰአቲቱም በጁመዓ ቀን ካልሆነ በቀር አትከሰትም።"

ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁሙዓ ቀን እንደሆነ ተናገሩ። የጁሙዓን ቀን ልዩ ከሚያደርገው ነገሮች መካከል: አላህ አደምን (ዐለይሂ ሰላም) የፈጠረው፣ ጀነት ውስጥ ያስገባው፣ ከጀነት አስወጥቶ ወደ ምድር ያወረደው በዚሁ ቀን ነው። ሰአቲቱም በጁሙዓ ቀን ካልሆነ በቀር አትከሰትም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ السويدية القيرقيزية اليوروبا الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከሁሉም የሳምንቱ ቀናቶች የጁሙዓ ቀን በላጭ መሆኑን እንረዳለን።
  2. በጁሙዓ ቀን መልካም ስራዎችን በማብዛት ላይ፣ የአላህን እዝነት ለማግኘት በመዘጋጀትና መአቱን በመከላከል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  3. ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሱት እነዚህ የጁመዓ ቀን መለዮዎች እንጂ የጁመዓን ቀን ደረጃ ለመጥቀስ ተብለው የተወሱ አይደሉም። የአደም ከጀነት መውጣትና የትንሳኤ ቀን መቆም ደረጃ ተደርገው አይቆጠሩም ያሉ ሲኖሩ፤ በሌላ በኩል ደሞ እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሱት ሁሉም ደረጃዎች ናቸው። የአደም ከጀነት መውጣት ከመልክተኞች፣ ከነቢያቶችና ከደጋጎች የሆኑ ዘሮችን ለማግኘት ሰበብ ሲሆን የትንሳኤ መቆም ደግሞ የደጋጎች ምንዳ ለመፍጠኑና አላህ ለነርሱ ያዘጋጀላቸውን መከበሪያ ለማግኘት ሰበብ ስለሆነ ያሉም አሉ።
  4. በዚህ ዘገባ ያልተጠቀሱ በሌላ ዘገባ ግን የተጠቀሱ የጁመዓ ቀን ሌሎች መለዮዎችም አሉ። ከነሱም መካከል: በጁመዓ እለት አላህ የአደምን ተውበት ተቀበለ፣ በጁመዓ እለት ሞተ፣ በዚህች ቀን አንድ አማኝ ባሪያ እየሰገደ አላህን አንዳች ነገር እየጠየቀ ይህቺን ሰዓት አያገኝም አላህ የጠየቀውን የሚሰጠው ቢሆን እንጂ የተባለላት አንዲት ሰዓት አለች።
  5. በዓመት ከሚገኙ ቀናቶች በላጩ ቀን የዐረፋ ቀን ነው። የእርድ ቀን ነው ያሉም አሉ። ከሳምንት ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁሙዓ ቀን ነው። በላጩ ምሽት ደግሞ የለይለተል ቀደር ምሽት ነው።