عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ:
«دَعُونِي مَا تَرَكْتُكُمْ، إِنَّمَا هَلَكَ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ بِسُؤَالِهِمْ وَاخْتِلَافِهِمْ عَلَى أَنْبِيَائِهِمْ، فَإِذَا نَهَيْتُكُمْ عَنْ شَيْءٍ فَاجْتَنِبُوهُ، وَإِذَا أَمَرْتُكُمْ بِأَمْرٍ فَأْتُوا مِنْهُ مَا اسْتَطَعْتُمْ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 7288]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ ((የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"በተውኳችሁ ላይ ተዉኝ። ከናንተ በፊት የነበሩት ህዝቦች የጠፉት በመጠየቃቸውና ነቢያቶቻቸውን በመቃረናቸው ነው። ከአንዳች ነገር የከለከልኳችሁ ጊዜ ራቁት፤ በአንድ ትእዛዝ ያዘዝኳችሁ ጊዜ ደሞ የቻላችሁትን ያህል ከርሱ ፈፅሙ!"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 7288]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሸሪዓ ድንጋጌዎች ለሶስት እንደሚከፈሉ ገለፁ። እነሱም: ዝም የተባለ፣ ክልከላዎችና ትእዛዛት ናቸው።
የመጀመሪያው: አላህና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለርሱ ዝም ያሉት ነው። ፍርድ ከሌለው የነገሮች መሰረቱ ግዴታ አለመሆኑ ነው። በርሳቸው ዘመን ስለአንዳች ስላልተከሰተ ነገር መጠየቅን መተው ግዴታ ነበር። ይህም በርሳቸው ላይ ግዴታ የሚያደርግ ወይም ክልክል የሚያደርግ መመርያ እንዳይወርድ ነው። አላህ የተዋት ለባሮቹ በማዘኑ ነውና። እርሳቸው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሞቱ በኋላ ግን ጥያቄው ፈታዋ በመጠየቅ መልኩ ወይም በሃይማኖቱ ጉዳይ የሚያስፈልገውን በመማር መልኩ የቀረበ ከሆነ ይህ የተፈቀደ ብቻ ሳይሆን የታዘዘበትም ጭምር ነው። ጥያቄን ተጨንቆ ፈጥሮና በግትርነት ከሆነ የጠየቀው ግን እዚህ ሐዲሥ ውስጥ መጠየቅን በመተው የተፈለገው ይህ አይነቱን ነው። ይህም በኒ ኢስራኤሎች ላይ የተከሰተው አምሳያ ወደመከሰት ስለሚያመራ ነው። ይህም ላም እንዲያርዱ በታዘዙ ወቅት ማንኛውንም የላም አይነት ቢያርዱ ትእዛዙን እንደፈፀሙ ይቆጠርላቸው ነበር። ነገር ግን እነሱ በመጠየቅ ሲያጠብቁት ትእዛዙም ጠበቀባቸው።
ሁለተኛው: ክልከላዎች ናቸው: ይህም መተዉ የሚያስመነዳ መተግበሩ የሚያስቀጣ ነው። ይህንንም ሙሉ ለሙሉ መራቅ ግዴታ ነው።
ሶስተኛው: ትእዛዝ ነው። እርሱም መስራቱ የሚያስመነዳ መተዉ የሚያስቀጣ ነው። በአቅም ልክ መተግበሩም ግዴታ ነው።