عَن عَلِيٍّ بْنِ أَبِي طَالِبٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
أَخَذَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ حَرِيرًا بِشِمَالِهِ، وَذَهَبًا بِيَمِينِهِ، ثُمَّ رَفَعَ بِهِمَا يَدَيْهِ، فَقَالَ: «إِنَّ هَذَيْنِ حَرَامٌ عَلَى ذُكُورِ أُمَّتِي، حِلٌّ لِإِنَاثِهِمْ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والنسائي وابن ماجه] - [سنن ابن ماجه: 3595]
المزيــد ...
ከዐሊይ ቢን አቢጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል:
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሐር በግራ እጃቸው ወርቅ በቀኝ እጃቸው በመያዝ ከዚያም እነሱን በእጃቸው ከፍ አደረጉና እንዲህ አሉ: "እነዚህ ሁለቱ ከኡመቴ በወንዶቹ ላይ ክልክል ናቸው። ለሴቶቹ ግን የተፈቀደ ነው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን ኢብኑ ማጀህ - 3595]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሐር ልብስ ወይም ቁራጩን በግራ እጃቸው ይዘው የወርቅ ጌጥ ወይም መሰል ነገር ደሞ በቀኝ እጃቸው ያዙና እንዲህ አሉ: ለወንዶች ሐርና ወርቅ መልበሳቸው ክልክል ነው። ለሴቶች ግን የተፈቀደ ነው።