عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لَيُوشِكَنَّ أَنْ يَنْزِلَ فِيكُمْ ابْنُ مَرْيَمَ حَكَمًا مُقْسِطًا، فَيَكْسِرَ الصَّلِيبَ، وَيَقْتُلَ الخِنْزِيرَ، وَيَضَعَ الجِزْيَةَ، وَيَفِيضَ المَالُ حَتَّى لاَ يَقْبَلَهُ أَحَدٌ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ። በናንተ ውስጥ የመርየም ልጅ ፍትሃዊ ዳኛ በቅርቡ ሆኖ ይወርዳል። መስቀልን ይሰባብራል፣ አሳማን ይገድላል፣ ግብርን ያነሳል፣ አንድም ሰው እስከማይቀበለው ድረስም ገንዘብ (ሀብት) ይበዛ።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመርየም ልጅ ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሰዎች መካከል በነቢያችን ድንጋጌ በፍትህ ሊፈርዱ መውረጃ ጊዜያቸው ቅርብ እንደሆነ ምለው ተናገሩ። በሚመጡ ወቅትም ክርስቲያኖች የሚያልቁትን መስቀል ይሰባብራሉ፤ ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አሳማዎችንም ይገድላሉ፤ ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ግብርንም ያስቀራሉ፤ ሰዎች ባጠቃላይ ወደ ኢስላም እንዲገቡም ይታገላሉ፤ ገንዘብ (ሀብት) ይትረፈረፋል አንዱ ከሌላው አይቀበለውም። ይህም ገንዘብ ከመብዛቱ፣ ሁሉም እያንዳንዱ እርሱ ዘንድ ባለው ገንዘብ የተብቃቃ ከመሆኑ፣ በረካ ሰፍኖ መልካምነትም ከመከታተሉ አኳያ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመጨረሻ ዘመን እንደሚወርዱ መረጋገጡንና የርሳቸው መምጣት የትንሳኤ ቀን ምልክት መሆኑን እንረዳለን።
  2. የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ድንጋጌ የሚሽር ሌላ ድንጋጌ እንደሌለ እንረዳለን።
  3. በመጨረሻ ዘመን ሰዎች ከገንዘብ ቸልተኛ ከመሆናቸውም ጋር የገንዘብ በረከት ግን እንደሚሰፍን እንረዳለን።
  4. በመጨረሻ ዘመን ዒሳ የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በኢስላም ሃይማኖት ስለሚፈርዱ ኢስላም ዘውታሪ ሃይማኖት መሆኑ መበሰሩን እንረዳለን።