+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنْ رَسُولِ اللهِ صلى الله عليه وسلم أنه قال:
«وَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ لَا يَسْمَعُ بِي أَحَدٌ مِنْ هَذِهِ الْأُمَّةِ يَهُودِيٌّ وَلَا نَصْرَانِيٌّ، ثُمَّ يَمُوتُ وَلَمْ يُؤْمِنْ بِالَّذِي أُرْسِلْتُ بِهِ إِلَّا كَانَ مِنْ أَصْحَابِ النَّارِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 153]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ያ የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ኡመት ውስጥ አንድም አይሁድ ይሁን ክርስቲያን ስለኔ ሰምቶ ከዚያም በዛ በተላኩበት ሳያምን የሚሞት የለም። ከእሳት ጓዶች መካከል ቢሆን እንጂ"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 153]

ትንታኔ

'ከዚህ ሕዝብ (ኡመት) ሆኖ የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጥሪ የደረሰውና ስለርሳቸው የሚሰማ ሆኖ ከዚያም በርሳቸው ሳያምን የሚሞት አንድም አይሁዳዊም ይሁን ክርስቲያን ወይም ሌላ እምነት ተከታይ የለም ዘልአለሙን የእሳት ሰው ቢሆን እንጂ።' ብለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht Oromisht Kannadisht الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልክተኝነት ዓለምን በሙሉ የሚጠቀልል መሆኑን፣ እሳቸውን መከተልም ግዴታ መሆኑን፣ በሳቸው ድንጋጌ ሁሉም ድንጋጌዎች መሻራቸውንም እንረዳለን።
  2. በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የካደ ሰው ከሳቸው ውጪ ባሉ ነቢያቶች የአላህ ሶላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይስፈንና እንደሚያምን መሞገቱ አይጠቅመውም።
  3. ስለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያልሰማና የኢስላም ጥሪ ያልደረሰው ሰው ተቀባይነት ያለው ምክንያት ስላለው የርሱ ጉዳይ በመጨረሻው አለም አላህ ዘንድ ነው።
  4. ነፍስ ልትወጣ ጉሮሮ ላይ እስካልደረሰች ድረስ ከባድ በሽታ ላይ ሆኖ እንኳ ቢሆን የሰለመ እስልምናው ከመሞቱ በፊት እስከሆነ ድረስ በኢስላም የሚገኘው ጥቅም የተረጋገጠ ነው።
  5. የከሀዲያንን ሃይማኖት ትክክለኛ እምነት አድርጎ ማሰብ ክህደት ነው። (ከነርሱም ውስጥ አይሁድና ክርስትና ይገኛሉ።)
  6. አይሁድና ክርስትናን በሐዲሡ ውስጥ መጠቀሳቸው ከነርሱ ውጪ ያሉትን አፅንኦት ለመስጠት ነው። ይህም አይሁድና ክርስቲያኖች መጽሐፍ እያላቸውም የነርሱ ጉዳይ እንዲህ ከሆነ ከነርሱ ውጪ መጽሐፍ የሌላቸው ደሞ በበለጠ መልኩ መንገድ የሐዲሡ መልእክት ውስጥ ይገባሉ። ስለሆነም ሁሉም በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እምነትና መመርያ ውስጥ መግባት ግዴታቸው ነው።
ተጨማሪ