عَنْ ثَوْبَانَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«أَفْضَلُ دِينَارٍ يُنْفِقُهُ الرَّجُلُ، دِينَارٌ يُنْفِقُهُ عَلَى عِيَالِهِ، وَدِينَارٌ يُنْفِقُهُ الرَّجُلُ عَلَى دَابَّتِهِ فِي سَبِيلِ اللهِ، وَدِينَارٌ يُنْفِقُهُ عَلَى أَصْحَابِهِ فِي سَبِيلِ اللهِ» قَالَ أَبُو قِلَابَةَ: وَبَدَأَ بِالْعِيَالِ، ثُمَّ قَالَ أَبُو قِلَابَةَ: وَأَيُّ رَجُلٍ أَعْظَمُ أَجْرًا مِنْ رَجُلٍ يُنْفِقُ عَلَى عِيَالٍ صِغَارٍ، يُعِفُّهُمْ أَوْ يَنْفَعُهُمُ اللهُ بِهِ وَيُغْنِيهِمْ.
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 994]
المزيــد ...
ከሠውባን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ሰውዬው ከሚያወጣው በላጩ ገንዘብ: ለቤተሰቦቹ የሚያወጣው ገንዘብ፣ ሰውዬው በአላህ መንገድ ለሚዘምትባት እንስሳ የሚያወጣው ገንዘብ፣ በአላህ መንገድ ለሚታገሉ ባልደረቦቹ የሚያወጣው ገንዘብ ነው። አቡ ቂላባህ እንዲህ አለ: በቤተሰብ ጀመሩ። ቀጥሎም አቡ ቂላባህ እንዲህ አለ "በታዳጊ ቤተሰቦቹ ላይ መፅውቶ የሚያብቃቃቸው ወይም አላህ በርሱ የሚጠቅማቸውና የሚያብቃቃቸው ከሆነ ሰውዬ የበለጠ ማንኛው ሰው ነው ትልቅ ምንዳ የሚያገኘው?!"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 994]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመመፅወት አቅጣጫዎችን ገለፁ። የሚመፀወትባቸው አቅጣጫዎች የተደራረቡ ጊዜም በእርሶ ላይ ግዴታ ከሚሆነው አንፃር ቅደም ተከተሉ ገለፁ። እጅግ አንገብጋቢና ወሳኝ በሆነውም ጀመሩ። እጅግ በጣም ብዙ ምንዳ የሚያስገኘው ገንዘብ አንድ ሙስሊም ወጪ ግዴታ ለሆነባቸው የሚመፀውተው ገንዘብ እንደሆነ ገለፁ። ለምሳሌ ሚስት፣ ልጅና የመሳሰሉት ቀጥሎ በአላህ መንገድ ለሚደረግ ጦርነት ለተዘጋጀ መጓጓዣ የሚወጣ ወጪ ነው። ቀጥሎም በአላህ መንገድ የሚታገሉ ለሆኑ ጓደኞቹና ባልደረቦቹ መመፅወት ነው።