عَن أَبِي أُمَامَةَ قَالَ: حَدَّثَنِي عَمْرُو بْنُ عَبَسَةَ رضي الله عنه أَنَّهُ سَمِعَ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«أَقْرَبُ مَا يَكُونُ الرَّبُّ مِنَ العَبْدِ فِي جَوْفِ اللَّيْلِ الآخِرِ، فَإِنْ اسْتَطَعْتَ أَنْ تَكُونَ مِمَّنْ يَذْكُرُ اللَّهَ فِي تِلْكَ السَّاعَةِ فَكُنْ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي] - [سنن الترمذي: 3579]
المزيــد ...
ከአቡ ኡማማ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዐምር ቢን ዐበሳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ እንደሰማቸው ነገረኝ:
"ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ አጋማሽ ነው። በዚህ ወቅት አላህን ከሚያወሱ መሆን ከቻልክ ሁን!"»
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3579]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጥራት የተገባው ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ ሲሶ በመሆኑ አንተ አማኝ ሆይ! በዚህ ወቅት ከሚያመልኩት፣ ከሚሰግዱ፣ ከሚያወሱ፣ በወንጀላቸው ከሚፀፀቱ ሰዎች መካከል ለመሆን ከተሳካልህና ከቻልክ በዚህ ወቅት አጅር መሸመትና መታገል የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ተናገሩ።