عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«أَقْرَبُ مَا يَكُونُ الْعَبْدُ مِنْ رَبِّهِ وَهُوَ سَاجِدٌ، فَأَكْثِرُوا الدُّعَاءَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 482]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 482]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ መሆኑን ገለፁ። ይህም ሰጋጅ ከሰውነቱ የላቀና የተከበረው አካሉን ለአላህ በሱጁድ ለመዋደቅ፣ ለመዋረድና ለመተናነስ ሲል መሬት ላይ የሚደፋ በመሆኑ ነው።
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሱጁድ ውስጥ ዱዓእ እንድናበዛም አዘዙን። በዚህም ንግግራዊም ድርጊታዊም መተናነስ ይሰባሰባሉ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አምልኮ ባሪያውን ወደ አላህ መቃረብን ትጨምርለታለች።
  2. ሱጁድ ዱዓእ ተቀባይነት ከሚያገኝበት ስፍራዎች መካከል አንዱ ስለሆነ ሱጁድ ውስጥ ዱዓእ ማብዛት እንደሚወደድ ተረድተናል።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (67)