عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بنِ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَيْسَ مِنَّا مَنْ لَطَمَ الخُدُودَ، وَشَقَّ الجُيُوبَ، وَدَعَا بِدَعْوَى الجَاهِلِيَّةِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1294]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ጉንጩን የመታ፣ አንገትያውን የቀደደ፣ በድንቁርና ጥሪ የተጣራ ከኛ አይደለም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1294]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአንዳንድ የድንቁርና ዘመን ሰዎች ተግባር አስጠነቀቁም ከለከሉም። እንዲህም አሉ: እነዚህ ከኛ አይደሉም:
የመጀመሪያው: ጉንጩን የመታ ነው። ጉንጭን የለዩት በአብዛኛው የሚፈፀመው እርሱ ስለሆነ ነው እንጂ የተቀሩትን የፊት ክፍልን መምታትም ክልከላው ውስጥ ይካተታል።
ሁለተኛው: ልብስ ላይ ጭንቅላት እንዲገባበት ተብሎ የሚከፈተውን (አንገትያ) ከትእግስት ማጣት ብዛት መቅደድ ነው።
ሶስተኛው: የድንቁርና ዘመን ጥሪዎችን መጣራት ነው። ለምሳሌ ያህል፦ ወዮልኝ፣ ወይኔ በጠፋው ማለት፣ ሙሾ ማውረድ፣ እየገጠሙ ማለቃቀስና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።