عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المؤْمنينَ رَضيَ اللهُ عنها قَالَتْ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي مَرَضِهِ الَّذِي لَمْ يَقُمْ مِنْهُ:
«لَعَنَ اللهُ الْيَهُودَ وَالنَّصَارَى، اتَّخَذُوا قُبُورَ أَنْبِيَائِهِمْ مَسَاجِدَ» قَالَتْ: فَلَوْلَا ذَاكَ أُبْرِزَ قَبْرُهُ، غَيْرَ أَنَّهُ خُشِيَ أَنْ يُتَّخَذَ مَسْجِدًا.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 529]
المزيــد ...
ከአማኞች እናት ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ድነው ያልተነሱበት በሆነው በሽታቸው ወቅት እንዲህ አሉ:
"አላህ አይሁድና ክርስቲያኖችን ረገመ። የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስጂድ አድርገው ያዙ። ዓኢሻም እንዲህ አለች: "ይህ (እርግማናቸው) ባልነበረ ኖሮ ቀብራቸው ይፋ ይሆን ነበር። ነገር ግን መስጂድ ተደርጎ እንዳይያዝ ተፈራ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 529]
የአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጠንቶባቸው በርሱ ምክንያት የሞቱበት በሆነው በሽታቸው ወቅት እንዲህ ይሉ እንደነበር ተናገረች: "አይሁዶችና ክርስቲያኖችን አላህ ይርገማቸው። ከእዝነቱ ያባራቸው። ይህም እነርሱ የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስጂድ አድርገው ስለያዙ ነው።" ይህም መቃብሩ ላይ መስጂድ በመገንባት ወይም እርሱ ዘንድ ወይም ወደርሱ ዞሮ በመስገድ ነው። ቀጥላም ዓኢሻ (ረዺየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - "ይህ የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ክልከላና ማስጠንቀቂያ ባይኖር ኖሮና እንዲሁም አይሁዶችና ክርስቲያኖች በነቢያቶቻቸው መቃብር ላይ እንደፈፀሙት በነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቀብር ላይም እንዳይፈፀም ሶሐቦች ባይፈሩ ኖሮ ቀብራቸው ይፋና ግልፅ ይሆን ነበር።" አለች።