عَنْ عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَا صَلَاةَ لِمَنْ لَمْ يَقْرَأْ بِفَاتِحَةِ الكِتَابِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 756]
المزيــد ...
ከዑባዳህ ቢን ሷሚት (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"የመጽሐፉን መክፈቻ (ፋቲሓን) ያላነበበ ሰው ሶላት የለውም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 756]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፋቲሓን ምዕራፍ በመቅራት ካልሆነ በቀር ሶላት ትክክለኛ እንደማትሆን ገለፁ። ፋቲሓ በሁሉም ረከዓዎች ከሚደረጉ የሶላት ማእዘናት መካከል አንዷ ናት።