عَنْ أَبِي عَبْدِ اللَّهِ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ الْأَنْصَارِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا:
أَنَّ رَجُلًا سَأَلَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: أَرَأَيْتَ إِذَا صَلَّيْتُ المَكْتُوبَاتِ، وَصُمْتُ رَمَضَانَ، وَأَحْلَلْتُ الحَلَالَ، وَحَرَّمْتُ الحَرَامَ، وَلَمْ أَزِدْ عَلَى ذَلِكَ شَيْئًا، أَأَدْخُلُ الجَنَّةَ؟ قَالَ: «نَعَمْ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [الأربعون النووية: 22]
المزيــد ...
ከአቡ ዓብደላህ ጃቢር ቢን ዐብደላህ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው:
«አንድ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- “ እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ) በዛም ላይ ምንም ካልጨመርኩ ጀነት እገባለሁን?” ነቢዩም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - “አዎን!” አሉት።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [الأربعون النووية - 22]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አምስቱን ግዴታ ሰላቶች የሰገደና አንድም ተጨማሪ ሰላት ጨምሮ ያልሰገደ ፣ ረመዳንን የፆመና ከዚህም ሱና ፆሞችን ያልጨመረ፣ (ሐላል) ፍቁድ ነገሮችን በፍቁድነታቸው አምኖ የተገበረና ሐራም ነገሮችን በክልክልነታቸው አምኖ የራቀ ጀነት እንደሚገባ ይገልጻሉ።