ምድቡ:
+ -


____

[] - []
المزيــد ...

ከአቡ ዓምር አቡ ዓምራ ነውም ተብሏል: ከሱፍያን ቢን ዐብደላህ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"የአላህ መልክተኛ ሆይ! በኢስላም ውስጥ ከርሶ ውጪ ስለርሱ አንድንም ሰው የማልጠይቀው የሆነን አንድን ንግግር ንገሩኝ አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ አምኛለሁ በል ከዚያም ቀጥ በል።' አሉኝ"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [الأربعون النووية - 21]

ትንታኔ

ሶሐቢዩ ሱፍያን ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ‐ ስለርሱ አንድንም ሳይጠይቅ እርሱን አጥብቆ የሚይዘው የሆነን የኢስላምን ሀሳቦች የጠቀለለ የሆነን ንግግር እንዲያስተምሩት ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጠየቀ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ "አላህ ብቻውን ጌታዬ፣ አምላኬ፣ ፈጣሪዬ፣ አጋር የሌለው በእውነት የሚመለከው ብቸኛ መሆኑን አረጋግጫለሁ። በል!" አሉት። ከዚያም ለአላህ ትእዛዝ የአላህን ግዴታዎች በመፈፀምና የአላህን ክልከላዎች በመተው ታዛዥ ይሁን፤ በርሱ ላይም ይዘውትር።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የእስልምና ሃይማኖት መሰረት በአላህ ጌትነት፣ ተመላኪነትና በስምና ባህሪያቶቹ ማመን ነው።
  2. ከማመን በኋላ ቀጥ የማለትን፣ በአምልኮ ላይ የመዘውተርና በዚህም ላይ የመፅናትን አንገብጋቢነት እንረዳለን።
  3. ኢማን ሥራዎች ተቀባይነት እንዲኖራቸው መስፈርት ነው።
  4. በአላህ ማመን ሲባል ማመን ግዴታ የሚሆንባቸውን እምነታዊ ጉዳዮችና መሰረቶችን፣ ይህንንም ተከትለው የሚመጡ የቀልብ ተግባራትን፣ በውስጥም ይሁን በውጪ ታዛዥነትንና እጅ መስጠትን ያጠቃልላል።
  5. "ኢስቲቃማ" (ቀጥ ማለት) ሲባል ግዴታዎችን በመስራትና ክልክሎችን በመተው ቀጥተንኛውን ጎዳና አጥብቆ መያዝ ማለት ነው።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأكانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ