ምድቡ:
+ -


____

[] - []
المزيــد ...

ከአቡ መስዑድ ዑቅባ ቢን ዓምር አልአንሷሪይ አልበድሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል:
"ሰዎች ከቀደምት ነቢያት ካገኟቸው ቃላት መካከል ካላፈርክ የፈለግከውን ስራ! የሚለው አንዱ ነው።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [الأربعون النووية - 20]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደዚህ ኡመት መጀመሪያ እስኪደርስ ድረስ ከቀደምት ነቢያት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲወራረሱትና በመካከላቸው ሲቀባበሉት ከነበሩ አደራዎች መካከል ልትሰራው የምትፈልገውን ስራ ተመልከት! ማድረጉ የማያሳፍር ስራ ከሆነ ስራው! የሚያሳፍር ስራ ከሆነ ተወው! የሚለው ይገኝበታል። ፀያፍን ከመስራት የሚከለክለው ሀፍረት ነው። ሀፍረት የሌለው ሰው በየትኛውም ፀያፍና ውግዝ ተግባር ውስጥ ይዘፈቃል።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሀፍረት የመልካም ስነ ምግባር መሰረት ነው።
  2. ሀፍረት ከነቢያት (ዐለይሂሙ ሰላም) ባህሪያት መካከል አንዱ ባህሪና ከነርሱ የተወሰደ መገለጫ ነው።
  3. ሙስሊም የሆነን ሰው የሚያስውበውና የሚያስጌጠውን እንዲሰራ፣ የሚያቆሽሸውና የሚያጎድፈውን ደሞ እንዲተው የሚያደርገው ሀፍረት ነው።
  4. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «ትእዛዙ መፍቀድንም ያቀፈ ነው: ማለትም አንዳች ነገር ለመስራት ብትፈልግ ብትሰራው ከአላህም ሆነ ከሰው የማያሳፍር ከሆነ ስራ! ያለበለዚያ አትስራው ማለት ነው። የእስልምና መሽከርከሪያ ዛቢያም ይኸው ነው። የዚህም ማብራሪያ በግዴታም ይሁን በፍቃደኝነት የመጡ ትእዛዛትን መተዉ የሚያሳፍር ነው። ሐራም ተደርገውም ይሁን ተጠልተው የተከለከሉ ክልከላዎችን ደግሞ መስራት የሚያሳፍሩ ናቸው። የተፈቀዱ ነገሮች ከሆኑ ግን ለመስራት የሚያሳፍሩም አሉ፤ ለመተው የሚያሳፍሩም አሉ። ስለዚህ ይህ ሐዲሥ አምስቱን ህግጋት አካትቷል ማለት ነው። ይህ ትእዛዝ ለዛቻ ነው የመጣው ያሉም አሉ። ማለትም: ሀፍረትክ ከተነሳ የፈለግከውን ስራ አላህ በስራህ ይመነዳሀልና።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأكانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ