ምድቡ:
+ -

عَنْ أَبِي العَبَّاسِ، عَبْدِ الله بْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ: كُنْت خَلْفَ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَوْمًا، فَقَالَ:
«يَا غُلَامِ! إنِّي أُعَلِّمُك كَلِمَاتٍ: احْفَظِ اللَّهَ يَحْفَظْكَ، احْفَظِ الله تَجِدْهُ تُجَاهَكَ، إذَا سَأَلْتَ فَاسْأَلِ اللهَ، وَإِذَا اسْتَعَنْتَ فَاسْتَعِنْ بِاَللهِ، وَاعْلَمْ أَنَّ الأُمَّةَ لَوْ اجْتَمَعَتْ عَلَى أَنْ يَنْفَعُوكَ بِشَيْءٍ لَمْ يَنْفَعُوكَ إلَّا بِشَيْءٍ قَدْ كَتَبَهُ اللَّهُ لَكَ، وَإِنِ اجْتَمَعُوا عَلَى أَنْ يَضُرُّوكَ بِشَيْءٍ لَمْ يَضُرُّوكَ إلَّا بِشَيْءٍ قَدْ كَتَبَهُ اللَّهُ عَلَيْكَ؛ رُفِعَتِ الأَقْلَامُ، وَجَفَّتِ الصُّحُفُ». وَفِي رِوَايَةِ غَيْرِ التِّرْمِذِيِّ: «احْفَظِ اللهَ تَجِدْهُ أَمَامَكَ، تَعَرَّفْ إلَى اللهِ فِي الرَّخَاءِ يَعْرِفْكَ فِي الشِّدَّةِ، وَاعْلَمْ أَنَّ مَا أَخْطَأَكَ لَمْ يَكُنْ لِيُصِيبَكَ، وَمَا أَصَابَك لَمْ يَكُنْ لِيُخْطِئَكَ، وَاعْلَمْ أَنَّ النَّصْرَ مَعَ الصَّبْرِ، وَأَنْ الفَرَجَ مَعَ الكَرْبِ، وَأَنَّ مَعَ العُسْرِ يُسْرًا».

[صحيح] - [رواه الترمذي وغيره] - [الأربعون النووية: 19]
المزيــد ...

ከአቡል ዐባስ ዐብደላህ ቢን ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «አንድ ቀን ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ኋላ ነበርኩ። እንዲህም አሉኝ:
"አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁ! የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ (አላህ) ይጠብቅሀል፤ የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜም በአላህ ታገዝ! እወቅ! ህዝብ ባጠቃላይ በአንዳች ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ለአንተ በፃፈልህ ነገር ካልሆነ በስተቀር አይጠቅሙህም። በአንዳች ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ለአንተ የፃፈብህ ካልሆነ በስተቀር አይጎዱህም። ብእሮቹም ተነስተዋል ፅሁፉም ደርቋል።"

-

ትንታኔ

ኢብኑ ዓባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ህፃን እንደነበሩና ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሚጋልቡበት ተፈናጥጦ ሳለ ለሱ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ እንዳሏቸው ይነግሩናል: እኔ አላህ በሷ የሚጠቅምህን ነገሮችንና ጉዳዮችን አስተምርሀለሁ። አላህ ትእዛዙንና ወደርሱ መቃረቢያን እየፈፀምክ በሚያገኝህ ሁኔታና ወንጀልና ሀጢዐቶች ውስጥም በማያገኝህ ሁኔታ የአላህን ትእዛዛት በመጠበቅና ክልከላውንም በመራቅ አላህን ጠብቅ! ይህንን ከፈፀምክ ምንዳህ በዓለማዊም በአኺራዊም ጣጣዎችህ የአላህ ጥበቃ የማይለይህና ወደየትም ብትዞርም የቸገረህን በመርዳት አላህ የሚጠብቅህ ትሆናለህ። አንዳች ነገር መጠየቅ የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር ማንንም አትጠይቅ! ለጠያቂዎች ልመና ምላሽ የሚሰጠው እሱ ብቻ ነውና። እገዛን የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር በማንም አትታገዝ! የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን ለመጥቀም ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ላንተ ከፃፈልህ በስተቀር አንድም ጥቅም እንደማታገኝና የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን በመጉዳት ላይ ቢሰባሰቡም አላህ ባንተ ላይ ከወሰነብህ በስተቀር ባንተ ላይ አንድም ጉዳት እንደማያደርሱብህ አንተ ዘንድ እርግጠኝነት ይኑር! ይህንን ጉዳይ የላቀውና የተከበረው አላህ ጥበቡና እውቀቱ ባስፈረደው መልኩ ፅፏታልም ወስኗታልም። አላህ የፃፈው ነገርም አይለወጥም። የአላህን ትእዛዛት በመጠበቅና ክልከላውን በመራቅ አላህን የጠበቀ ሰው አላህ ባሪያው ያለበትን ሁኔታ ያውቃልና እርሱን በመርዳትና በማገዝ ከፊትለፊቱ ይሆናል። ሰው በድሎት ወቅት አላህን ከታዘዘ አላህም በጭንቁ ወቅት ስኬትና መውጫ መንገድን ያበጅለታል። ሁሉም ሰው አላህ በወሰነለት መልካምም ይሁን መጥፎ ነገር መውደድ አለበት። ከችግሮችና ፈተናዎች ጋርም አንድ ባሪያ ትእግስትን መያዝ አለበት። ትእግስት የስኬት ቁልፍ ነው። ችግር በበረታ ወቅት ከአላህ የሆነ ስኬት ይመጣል። አላህ ችግርን ሲያመጣ ድሎትንም ያስከትልበታል።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አንድ ሰው ችግር ባጋጠመው ጊዜ ድሎት መጠባበቅ እንዳለበት መነገሩ ታላቅ ብስራት ነው።
  2. አንድን ባሪያ መከራ ቢያጋጥመውና የፈለገው ጉዳይ ቢሰናከልበት "እወቅ! የሳተህ ነገር ሊያገኝህ አልነበረም። ያገኘህ ነገርም ሊስትህ አልነበረም።" የሚለው የሐዲሡ ጥቅስ ያፅናናዋል። የመጀመሪያው አረፍተ ነገር መከራ ሲያጋጥም የሚያፅናና ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ያቀደው ጉዳይ ሲሰናከል የሚያፅናና ነው።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht المجرية التشيكية الموري الولوف Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ