عَنْ أَبِي يَعْلَى شَدَّادِ بْنِ أَوْسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ اللهَ كَتَبَ الْإِحْسَانَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ، فَإِذَا قَتَلْتُمْ فَأَحْسِنُوا القِتْلَةَ، وَإِذَا ذَبَحْتُمْ فَأَحْسِنُوا الذِّبْحَةَ، وَلْيُحِدَّ أَحَدُكُمْ شَفْرَتَهُ، وَلْيُرِحْ ذَبِيحَتَهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [الأربعون النووية: 17]
المزيــد ...
ከአቡ የዕላ ሸዳድ ቢን አውስ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦
«አላህ ሁሉም ነገር ላይ መልካምነትን ጽፏል፤ ስትገድሉም አሳምራችሁ ግደሉ፤ ስታርዱም አሳምራችሁ እረዱ፤ አንዳችሁ ስለቱን በደንብ ይሞርድና እንሰሳውን ቶሎ ይገላግል።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [الأربعون النووية - 17]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ በኛ ላይ በሁሉም ነገሮች ኢሕሳንን ግዴታ እንዳደረገ ተናገሩ። ማሳመር (ኢሕሳን) ማለት በአምልኮውም ውስጥ፣ መልካምን ሲፈፅምም፣ ከፍጡራን ላይ ጎጂን ነገር ሲያስወግድም ዘውትር አላህ ያየኛል ማለት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በመግደልና በማረድ ውስጥ ማሳመርም አንዱ ነው።
በመግደል ኢሕሳን ሲባል በቂሷስ (ሸሪዐዊ የቅጣት ብይን ለምሳሌ የገደለ መገደል) ተፈፃሚነት ወቅት: ለመግደል ገሩን፣ ቀላሉንና የተገዳዩን ነፍስ በፍጥነት ሊያወጣ የሚችለውን መንገድ በመምረጥ ነው።
በእርድ ማሳመር ሲባል ደግሞ እንስሳ በምናርድበት ወቅት ነው። ይህም መሳሪያውን በደንብ በመሞረድ ፣ የሚታረደው እንስሳ እያየ ፊት ለፊቱ ባለመሞረድና ሌላ እርዱን የሚመለከት እንስሳ ቦታው ላይ እያለ ባለማረድ ለእንስሳ በማዘን ነው።