____
[] - []
المزيــد ...
የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አገልጋይ ከነበረው ከአቡ ሐምዛ አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [الأربعون النووية - 13]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለነፍሱ የሚወደውን አምልኮዎችና ሃይማኖታዊም ይሁን ዱንያዊ መልካም ነገሮችን ለወንድሙ እስከሚወድ ድረስ፤ ለነፍሱ የሚጠላውንም ለርሱ እስኪጠላ ድረስ ለአንድ ሙስሊም የተሟላ ኢማን እንደማይረጋገጥ ገለፁ። በሙስሊም ወንድሙ ላይ የዲን ጉድለት ከተመለከተም ለማስተካከል ይታገላል። በርሱ ላይ መልካምን ከተመለከተም ያበረታዋል፣ ያግዘዋል፣ የዲኑን ወይም የዱንያውን ጉዳይም ይመክረዋል።