عَنْ أَبِي مُـحَمَّدٍ الحَسَنِ بْنِ عَلِيِّ بْنِ أَبِي طَالِبٍ - سِبْطِ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَرَيْحَانَتِهِ-، قَالَ: حَفِظْتُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«دَعْ مَا يَرِيبُك إلَى مَا لَا يَرِيبُكَ».
[صحيح] - [رواه الترمذي والنسائي] - [الأربعون النووية: 11]
المزيــد ...
የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የልጅ ልጅና መአዛቸው ከሆነው ከአቡ ሙሐመድ ሐሰን ቢን ዓሊይ ቢን አቢጧሊብ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይህንን ሸምድጃለሁ:
"የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ!"
-
ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ክልክል ነው ወይስ አይደለም፣ ሐላል ነው ወይስ ሐራም ነው እያልክ የምትጠራጠርበት ንግግርና ተግባር በመተው መልካምነቱንና ፍቁድነቱን እርግጠኛ ወደሆንክበትና ወዳልተጠራጠርክበት መሄድን አዘዙ።