+ -

عن جندب رضي الله عنه قال:
سَمِعْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَبْلَ أَنْ يَمُوتَ بِخَمْسٍ وَهُوَ يَقُولُ «إِنِّي أَبْرَأُ إِلَى اللهِ أَنْ يَكُونَ لِي مِنْكُمْ خَلِيلٌ فَإِنَّ اللهَ تَعَالَى قَدِ اتَّخَذَنِي خَلِيلًا كَمَا اتَّخَذَ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا، وَلَوْ كُنْتُ مُتَّخِذًا مِنْ أُمَّتِي خَلِيلًا لَاتَّخَذْتُ أَبَا بَكْرٍ خَلِيلًا! أَلَا وَإِنَّ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ كَانُوا يَتَّخِذُونَ قُبُورَ أَنْبِيَائِهِمْ وَصَالِحِيهِمْ مَسَاجِدَ، أَلَا فَلَا تَتَّخِذُوا الْقُبُورَ مَسَاجِدَ! إِنِّي أَنْهَاكُمْ عَنْ ذَلِكَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 532]
المزيــد ...

ከጁንዱብ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡
"ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመሞታቸው አምስት (ሌሊቶች) በፊት እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡- ' እኔ ከናንተ መካከል ፍፁም ወዳጅ ከመያዝ ወደ አላህ እጥራራለሁ። ምክንያቱም የላቀው አሏህ ኢብራሂምን ፍፁም ወዳጅ አድርጎ እንደያዘው ሁሉ እኔንም ፍፁም ወዳጅ አድርጎ ይዞኛልና። ከኡመቴ መካከል ፍፁም ወዳጅ አድርጌ የምይዝ ብሆን ኖሮ አቡበከርን ነበር ፍፁም ወዳጅ አድርጌ የምይዘው። አዋጅ! እነዚያ ከናንተ በፊት የነበሩት የነብያቶቻቸውንና የፃድቃኖቻቸውን መቃብር መስገጃ ስፍራ አድርገው ይይዙ ነበር። አዋጅ! መቃብርን መስገጃ ስፍራ አድርጋችሁ አትያዙ! እኔ እየከለከልኳችሁ ነው።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 532]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአላህ ዘንድ ያላቸውን ደረጃ አሳወቁ፤ ልክ እንደ ኢብራሂም ዐለይሂ ሰላም እሳቸውም ላእላይ እርከን የደረሰ ውዴታ መጎናፀፋቸውንም ተናገሩ። ልባቸው በአላህ ውዴታ፣ ማላቅና ማወቅ ስለተሞላ ከአሏህ ውጭ ፍፁም ወዳጅ ሊኖራቸው እንደማይችልም ገለፁ። ከፍጡራን መካከል ፍፁም ወዳጅ የሚይዙ ቢሆኑ ኖሮ ያ ሰው አቡበከር አስሲዲቅ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ይሆን እንደነበረም ተናገሩ። ከዚያም አይሁዶችና ክርስቲያኖች የነቢያቶቻቸውንና የፃድቃኖቻቸውን መቃብር ከአላህ ውጪ ወደምትመለክ ጣኦታዊ የአምልኮ ስፍራ በመለወጥ እንዲሁም የፃድቃኖችና ነቢያቶች መቃብር ላይ መስገጃና ቤተ መቅደሶችን በመገንባት የፈፀሙትን ልክ ያለፈ የውዴታ ድንበር ከማለፍ አስጠነቀቁ። አስከትለውም ኡመታቸውም የነሱን አይነት ድርጊት እንዳይፈፅሙ ከለከሉ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አቡበክር ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ ያላቸውን ደረጃ፤ ከሶሓቦችም ሁሉ በላጩ እርሳቸው መሆናቸውን፤ ከረሱል ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም በኋላ በርሳቸው የመሪነት ቦታ ለመተካት ይበልጥ የተገቡትም እርሳቸው መሆናቸውን እንረዳለን።
  2. በመቃብር ላይ መስገጃ መገንባት ያለፉት ህዝቦች ከሚፈፅሟቸው ውግዝ ተግባራት መካከል ነው።
  3. መቃብርን የአምልኮ ስፍራ አድርጎ መያዝ፣ መቃብር አጠገብም ሆነ ወደርሷ ዞሮ መስገድ፣ ወይም በላያቸው ላይ መስገጃ ወይም ጉልላት መስራት ወደ ሽርክ ሊያደርስ ስለሚችል ተከልክሏል።
  4. በፃድቃን ላይ ድንበር ማለፍ ወደ ሽርክ ሊያደርስ ስለሚችል መጠንቀቅ ይገባል።
  5. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከመሞታቸው አምስት ቀናት ቀደም ብለው ማስጠንቀቃቸው ያስጠነቀቁት ጉዳይ ያለውን አደገኝነት ያሳያል።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأكانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ተጨማሪ